የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከመተከል በግፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች ለምግብነት የሚውል 66 ኩንታል ፊኖ ዱቄት በዛሬው ዕለት ልኳል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም…

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከመተከል በግፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች ለምግብነት የሚውል 66 ኩንታል ፊኖ ዱቄት በዛሬው ዕለት ልኳል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የደብረ ማርቆስ ከተማ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ከማህበረሰቡ ያሰባሰበውን ድጋፍ ባለፉት ወራት ህግ በማስከበር ስራ ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ሦስት ጊዜ የላከና ያስረከበ ሲሆን፤ለገና በዓል መዋያ በከተማዋ ለሚገኙ የአድማ ብተና ፖሊስና ልዩ ሃይል አባላት ሁለት ሰንጋና ሁለት ሙክት ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ የደብረ ማርቆስ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ዛሬም የዚህ አንድ አካል የሆነውን ለ5ኛ ገዜ 66 ኩንታል ፊኖ ዱቄት ነው በመተከል ዞን በግፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች እንዲደርስ ድጋፉ የተላከው፡፡ በቀጣይም ይህ ድጋፍ በቂ ስለማይሆን ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡ በዛሬው ዕለት በአጠቃላይ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች 4መቶ 72 ኩንታል የምግብ እህል ከመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲውል ተብሎ መላኩን የደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽን ዘገባ አመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply