የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የህልውና ዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል በመሰብሰብ ላይ መሆናቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አ…

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የህልውና ዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል በመሰብሰብ ላይ መሆናቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለህልውና ዘመቻው ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ሁለ-ገብ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞች በየዕለቱ ስንቅ በማዘጋጀት እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ወረዳዎችና ቀበሌዎች ከ400 በላይ መምህራንና ሰራተኞች ህብረተሰቡን በማንቃትና በማደራጀት ለህልውና ዘመቻው ህሊናዊና አካላዊ ዝግጅት እንዲያደርግ ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ ተገልጧል፡፡ ከዚሁ ተግባር ጎን ለጎን ደግሞ ወቅቱ ሰብል የሚደርስበት በመሆኑ የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል የመሰብሰብ ተግባር ከህዳር 14/2014 ጀምሮ በተጠናከረ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ሰብል የመሰብሰብ ተግባሩም በዩንቨርሲቲው የተለያዩ ኮሌጆች፣ ዳይሬክቶሬቶችና የስራ ክፍሎች እየተመራ ባለፉት የስራ ቀናት በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነራታ እና ቸርተከል ቀበሌዎች እንዲሁም በአዋበል ወረዳ የሰብል ስብሰባ ስራው የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ የስራ ቀናት የሰብል ስብሰባ ስራው በሌሎች የዘማች አርሶ አደሮች ማሳ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያለው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply