
የደብረ ማርቆ ከተማ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ ዛሬ ጀመረች “በኃይል ሱቆችንም ሆነ ተሽከርካሪዎች እንዲንቀሳቀሱ የሚሞከር የመንግስት ታጣቂም ይሁን በፋኖ ስም ታጥቆ በከንቲባው ትዕዛዝ የሚንቀሳቀስ አካል ለዓለም ህዝብ የሚጋለጥ መሆኑን አዎቆ አደብ ሊገዛ ይገባል” ሲል ህዝባዊ ኃይሉ አስጠንቅቋል። በደብረ ማርቆስ ከተማ በፋኖ ስም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የብአዴን ታዛዦች እንዳሉ ታውቋል።ቡድኑን የሚመራው ግለሰብ ተለይቷል።ህዝብ የሚያደርገውን ትግል ለመረበሽ የሚሞክሩ ከሆነ በቀጣይ የመሪውን፣ የአባላቱን እና የቡድኑን ስያሜ ለህዝብ ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናስታውቃለን። “የአማራ ህዝብ ሁነኛ የፖለቲካ ወኪል አግኝቶ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የዘር ማጥፋቱና ማፅዳቱ እስካልቆመ ድረስ፣ጥቅሙ እና መብቱ እስካልተከበረ ድረስ ከዚህ በኋላ የሚቆም ትግል የለም” ሲል ህዝባዊ ኮሜቴው ገልጿል። ትግሉን እራሱ ህዝቡ ተቀብሎ መምራቱ እና ለገዥው ሥርዓት ባለመታዘዝ ለመብቱ መቆሙን ህዝባዊ ኮሚቴው አድንቆ በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
Source: Link to the Post