የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገ/ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው መገደላቸውን የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገለጸ።በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ የደብረ  ቅዱሳን…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/kH7nGMDed5PQkRKvTFV_cF-rWG0w7zGtK9MRE5tgBKhf6tksvmCkFi3wcf5LCnPCpAI5QqdjgvFqSyiL4bdseYhdWXIzRj-x35rpWfzIlAtgogEcTWhUG3qO4DnScOaszsQBP5uRMSliMyHxG-OmiaHhrrlMtVY8kcIA5o__cVre8ZVWJgj2g0COUiAgJ8kv3eY_dPdeVTR3TlOPYcx13dyESIrplHtN9KPxDsiDQKtO4qDPZznAk1bFDIXuNso6doQ6wU2yWMtF4IRN2X1Nn-clrOM4o_SpHdOs15G06A1o0icudlq8xuOdOS2wlTaE9c2zQMIo1C6nT-_2J7jrvA.jpg

የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገ/ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው መገደላቸውን የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገለጸ።

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ የደብረ  ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 2 አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለጊዜው ” ማንነታቸው አልታወቀም ” በተባሉ አካላት መገደላቸው ተነግሯል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው ፤ ግድያው የተፈፀመው ትናንት መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ገደማ መሆኑን የአካባቢው ምዕመናን እንደነገሩት ገልጿል።

በተፈጸመው በዚህ ግድያ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን  አገልጋይ የሆኑት አንድ መሪጌታና ዲያቆንን ጨምሮ 5 የቤተሰብ አባሎቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተገልጿል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው ፥ በዶዶላ ከተማ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን አስታውሷል።

መጋቢት 17  ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply