የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለ4 ቀናት የሚቆይ አውደ ርዕይ እንደሚያደርግ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  የካቲት 25 ቀ…

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለ4 ቀናት የሚቆይ አውደ ርዕይ እንደሚያደርግ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 25 ቀ…

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለ4 ቀናት የሚቆይ አውደ ርዕይ እንደሚያደርግ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብት እና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለ4 ቀናት የሚቆይ አውደ ርዕይ እንደሚያደርግ አስታውቋል። የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብት እና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ በመተባበር ከየካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የምርምር ስራዎች፣ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች እና የመጻሕፍት ዐውደ ርዕይ የሚቀርብበት ታላቅ መርሀ-ግብር አዘጋጅቶ እየጠበቀ መሆኑን ገልጧል። መርሀ ግብሩም “ተምሳሌት ሴቶች ከመዛግብትና መጻሕፍት ገጾች” በሚል መሪ ቃል ይቀርባል። በመጨረሻም “የተከበራችሁና የተወደዳችሁ ተማሪዎች፣ መምህራንና ሰራተኞች በእለቱ ተገኝታችሁ መርሀ ግብሩን እንድትከታተሉ እየጋበዝን፣ ለመታደም ያግዛችሁ ዘንድ ከባህል ጥናት ዳይሬክቶሬት የተላከውን ዝርዝር መርሀ ግብር እየተከታተላችሁ እንድትቆዩ እንጋብዛለን።”የሚል መልዕክቱን ዩኒቨርስቲው አስተላልፏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply