You are currently viewing የደብረ ኤልያስ ሥላሴ ገዳም በፋሽስት የኦህዴድ ጨፍጫፊ ስራዊት በከባድ መሳሪያ እየተደበደበ እንደሆነ እና በዛሬው የገዳሙ ጉልላት በከባድ መሳሪያ ተመቶ መውደቁን የአማራ ወጣቶች ማህበር አረጋ…

የደብረ ኤልያስ ሥላሴ ገዳም በፋሽስት የኦህዴድ ጨፍጫፊ ስራዊት በከባድ መሳሪያ እየተደበደበ እንደሆነ እና በዛሬው የገዳሙ ጉልላት በከባድ መሳሪያ ተመቶ መውደቁን የአማራ ወጣቶች ማህበር አረጋ…

የደብረ ኤልያስ ሥላሴ ገዳም በፋሽስት የኦህዴድ ጨፍጫፊ ስራዊት በከባድ መሳሪያ እየተደበደበ እንደሆነ እና በዛሬው የገዳሙ ጉልላት በከባድ መሳሪያ ተመቶ መውደቁን የአማራ ወጣቶች ማህበር አረጋግጧል ‼️ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአማራ ህዝብ ላይ ወረራ የፈፀመው የኦህዴድ /ኦነግ ስራዊት የመከላከያ ልብስ በመልበስ በህዝባችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል ።ይህ እንቅሶቃሴ በአራቱም የአማራ ግዛቶች፦ በሸዋ ፣በጎጃም ፣በጎንደር እና በወሎ አጠናክሮ ቀጥሎበታል ። ይህ ወራሪና ጨፍጫፊ የኦነግ አማራ ጠል ፣ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ጠል እና የነባር እስልምና ሀይማኖት ጠል የሆነ ሰራዊት ከሰሞኑ ለሆዳቸው ባደሩ ፣በአማራ ህዝብ ላይ በተጣበቁ ደም መጣጭ መዥገሮች የምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም የብልፅግና ሎሌዎች ፤የፀጥታ አካላት መንገድ መሪነት ወደ ደብረ ኤልያስ ፣የጁቤ ፣ኮርክ፣ጃዊ እዲሁም ወደ ተለያዩ የጎጃም ክፍሎች ተሰማርቶ ከፍተኛ ጥቃት እየፈፀመ እንደሆነ ከአካባቢው ከሚገኙ የማህበራችን መዋቅሮች አረጋግጠናል ። ወራሪው ሀይል ከትላንት ጀምሮ በንፁሃን የአማራ ወገኖቻችን ፣በደብረ ኤልያስ ገዳማውያን ላይ በከባድ መሳሪያ በታገዘ ሁኔታ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፍቶ ይገኛል ።በዚህ የፋሽስቱ ስራዊት አስነዋሪ ተግባር ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ።የገዳሙ ጉልላት በደሽቃ ፣በብሬል እና በሌሎች ከባድ መሳሪያ ተመትቶ ወድቋል ፤ጣሪያው ተበሳስቷል እንዲሁም በስፍራው የሚገኙ ካህናት ፣ገዳማውያን እና ፀበልተኞች በጥይት ተመተዋል ። ከዚህ ቀደም ከሁለት ወር በፊት ይህ የፋሽስት ስራዊት በስፍራው “ፋኖ ይደበቃል” በሚል ተልካሻ ምክንያት በተመሳሳይ በከፈተው ጦርነትና ወረራ በርካታ ካህናትና፣መነኮሳት እና ፀበልተኞች መገደላቸው የሚታወስ ነው ። በመሆኑም የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) በደብረ ማርቆስ ፣አማኑኤል ፣ደንበጫ ፣ደብረ ኤልያስ ፣ደጀን ፣ፍኖተ ሰላም ፣ቢቸና ፣ደብረ ወርቅ ጨምሮ በመላው ጎጃም የምትገኙ የአማራ ወጣቶች ማህበር አባላትና ደጋፊዎች ፣መላው የአማራ ህዝብ እንዲሁም ሁሉም የአማራ ህዝባዊ ሀይል (ፋኖ) አባላት እራስን የመከላከልና ማንነት የማስከበር እንቅስቃሴ እንዲደረግ ማህበራችን አስቸኳይ ጥሪውን ያስተላልፋል ። ራስን የመከላከል በዓለማዊውም ፣በመንፈሳዊው የእምነት ህግጋቶች የሚፈቅዱት የውዴታ ግዴታ የሆነ ፣ራስን የመካለከል ፣ማንነትን የማስቨጠበቅ ፣የሀይማኖት ተቋማትን የማስከበር እንቅስቃሴ ውስጥ ሁሉም እንዲገባ ጥሪያችን እናስተላልፋለን በተጨማሪም የገባውን ወራሪ የኦነግ ስራዊት መግቢያና መውጫው እንዲዘጋ እንዲሁም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ የአማራ ወጣቶች ማህበር የከበረ ጥሪውን ያስተላልፋል ። ህልውናችን በክንዳችን ፤ትግላችን ለህልውናችን‼️ የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply