
የደብረ ወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ2ዐ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገለት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ የሚገኘው የደብረ ወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የአካባቢው ተወላጆች ለህብረተሰቡ በተሟላ መልኩ የህክምና አገልግሎት መስጠት እንዲችል ከ2ዐ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርገዋል። በድጋፉ የመመርመርያ ማሽኖች እና ለህክምና እገዛ የሚያደርጉ በርካታ ቁሳቁሶች ድጋፋ የተደረጉ ሲሆን ይህም ተጠናክሮ እንሚቀጥል ተገልጿል ያለው አማራ ኮሙኒኬሽን ነው።
Source: Link to the Post