የደንበጫ-ፈረስ ቤት-ሰከላ እና ቢቡኝ የሚያገናኝ አገናኝ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጀመረ።    አሻራ ሚዲያ የካቲት 22/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስ…

የደንበጫ-ፈረስ ቤት-ሰከላ እና ቢቡኝ የሚያገናኝ አገናኝ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጀመረ። አሻራ ሚዲያ የካቲት 22/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስ…

የደንበጫ-ፈረስ ቤት-ሰከላ እና ቢቡኝ የሚያገናኝ አገናኝ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጀመረ። አሻራ ሚዲያ የካቲት 22/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት የማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ ተከናውኗል። የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታው 70 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፤ በመንግሥት ወጭ የሚሸፈን 1 ነጥብ 79 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል ብሏል። ሀገር በቀል ተቋራጩ የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ግንባታውን ያከናውናል። ግንባታውም በ3 ዓመት ጊዜ እንዲያጠናቅቅ የጊዜ ገደብ ተሰጥቶታል። የመንገዱን ጥራት በመቆጣጠር እና በማማከር የሚሳተፈው ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ የተባለው ሀገር በቀል አማካሪ ድርጅት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ከደንበጫ -ሰከላ 59 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው የቢቡኝ ወረዳ የሚያገናኘው መንገድ ደግሞ 11 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡ መንገዱ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ይገነባል ተብሏል፡፡ የመንገድ ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ በደጀን ደብረማርቆስ በዳንግላ አድርጎ ባሕርዳር የሚገባው መንገድ እና በአዲስ አበባ ደጀን ደብረወርቅ መርጡለ ማርያም ወደ ባሕርዳር የሚዘልቀውን ሌላኛውን ዋና መንገድ በአቋራጭ የሚያገናኝ ግዙፍ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው እንደሆነም ተመላክቷል፡፡ የመንገዱ መገንባት የአካባቢው ከፍተኛ የግብርና ምርቶች ፣ የቁም እንስሳት እና የቀርከሃ ምርት ውጤቶች የሚገኝበት በመሆኑ ትራንስፖርትን ተጠቅመው በፍጥነት ወደ ማዕከላዊ ገበያ በማድረስ አምራቹን ከሸማቾች ጋር በማገናኘት ከምርታቸው ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply