የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በየቦታው የሚለጠፉ ህገወጥ ማስታወቂያዎች አታሚውንና ምርቱን የሚያስተዋውቀው ድርጅን አፈላልጎ መቅጣት እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮም…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/WAklrlqfE4sECrb84mVihOd-8VEJvYKOFwSpnvkEtnmn81cVf0ctpdtLNd7YQSnTGOFOnbvKh759rE0gRpRsuQ26Y26-4WNd8tA1nb1OG6cH8-mRPpSaeEOHw5MlV_3iseDb4VMEaSURM286tHcCLT4BLYM6XctJeE_Zmg3oLOKY0RfBcH3fXXd7ILR03hcIDpotR4ycuLppNQM9phemNUaPCEPgrclSu7PsWQ5KpLEmbDmwLVFz2aB-cu8RStRDQyEifziahLY-cJ31wRAWDUMA7LtMZP96Ra13JYvpmyP88m-ufpcKcBNmzGlI6-KblRXMgctAv0M29lrYOr_d_A.jpg

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በየቦታው የሚለጠፉ ህገወጥ ማስታወቂያዎች አታሚውንና ምርቱን የሚያስተዋውቀው ድርጅን አፈላልጎ መቅጣት እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ምስራች ግርማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት አታሚውና ምርቱን የሚያስተዋውቀው ድርጅትን አፈላልጎ ተገቢውን ቅጣት የመቅጣት ስራዎችን ለመስራት እቅድ ተይዟል፡፡

በከተመዋ የስልክና የመብራት ምሰሶዎች ላይ አጥርና በየግድግዳዎች የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ህጋዊ ፍቃድ ያልተሰጣቸው መሆናቸውን አቶ ምስራች ተናግረዋል፡፡

ህገወጥ የሆኑ ማስታወቂያዎች በብዛት የሚለጠፋት ደንብ አስከባሪዎች በማይኖሩበት እና ጨለማን ተገን በማድረግ በመሆኑ ስራችን ላይ እንቅፋት ሆኖብናል ብለዋል፡፡

በ2016 ዓ.ም በመጀመሪያ ስድስት ወር 2 መቶ 54 ሺ 2መቶ 25 ህገወጥ ማስታወቂያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል ።
እርምጃዎች እየተወሰዱ ቢሆንም ድርጊቱ ግን ሊቆም አለመቻሉንም ተናግረዋል።

ህብረተሰቡም በድብቅ ማስታወቂያዎችን የሚያሰራጩ አካላትን ሶመለከት ለደንብ ማስከበር ባለስልጣን ወይም በነፃ ስልክ መስመር 9995 ላይ በመደወል ህገወጥ ስራዎችን በማጋለጥ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚገባም ተናግረዋል።

በሐመረ ፍሬው

የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply