የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፓርላማ አባላት በምክር ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ተደባደቡ።የፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቴሽኬዲ እና የቀድሞውን ርዕሰ ብሄር ጆሴፍ ካቢላ ደጋፊዎችን እንዲገላግል ፖሊስ መጠራቱም…

https://cdn4.telesco.pe/file/TWah2ROp4IHkApFngH090JsLj2J8sCcXxuyONkZSADG7JwfQ1VIZ0FpGwGUQJKjkufPHnhAXDC2Nkp1_30FB7ef6BgHbSKNbPBjRa28AfmhmwopLkje1z7FGMYPAmwkBGdEg1de8JPGXeVHNiWepq1IoBRE0c148SvHxWMs6UyW5IibE0wJ3xJj1YurYhXkEgx90DaT45REyN69K80cL9ps9M3H9TUHhsP3TC15PzucnUU7Llt-HkUqDxDJlHIEMee_fymk8JmP6k8KQJK5l96Ij_IbGGojPn_CpIl_O9G-czM-OeRNn3V5wjZUUhZOKP2kEYNY_KZqEOpr980uYwg.jpg

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፓርላማ አባላት በምክር ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ተደባደቡ።

የፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቴሽኬዲ እና የቀድሞውን ርዕሰ ብሄር ጆሴፍ ካቢላ ደጋፊዎችን እንዲገላግል ፖሊስ መጠራቱም ተነግሯል፡፡
ተቀናቃኞቹ ቡድኖች በተወራወሯቸው ቁሳቁሶች ሶስት ሰዎች ጉዳት እንደ ደረሰባቸው AFP ዘግቧል፡፡

በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ በሚገኘው ፓርላማ ፊት ለፊት የተሰበሰበውን ህዝብ ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ጥቅም ላይ መዋሉም ተነግሯል፡፡

ብጥብጡ የተነሳው ፕሬዝደንት ቴሽኬዲ ፤የካቢላ ደጋፊዎች ለወራት የፈጠሩትን ፖለቲካዊ እንቅፋት ለመቅረፍ የሚያግዛቸውን ዕቅድ ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው ፡፡

ፕሬዘዳንቱ በቴሌቪዥን በተላለፈው መልዕክት አስፈላጊ ሆኖ ካገኙት ምክርቤቱን ለመበተን መዘጋጀታቸውን ተናግረው ነበር፡፡

በቀድሞው ፕሬዝዳንት ደጋፊዎች በተሞላው ምክር ቤቱ አዲስ አብላጫ ወንበር ያለው ጥምረት ለመፍጠር የሚያግዛቸው ባለስልጣን እንደሚሾሙም ተናግረዋል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply