You are currently viewing የዲሲ አገራዊ ጥሪ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ ይህ አገራዊ ጥሪ May 22 2022 በዋሽንግተን ዲሲ Washington Renai…

የዲሲ አገራዊ ጥሪ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ይህ አገራዊ ጥሪ May 22 2022 በዋሽንግተን ዲሲ Washington Renai…

የዲሲ አገራዊ ጥሪ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ይህ አገራዊ ጥሪ May 22 2022 በዋሽንግተን ዲሲ Washington Renaissance Hotel በተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የተላላፈው ሀገራዊ ጥሪ ነው። የተነበበው በኤርሚያስ ለገሠ ነው። ቪዲዮውንም አያይዘናል። እኛ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የምንኖር ኢትዮጵያዊያን፣ አገራችን ኢትዮጵያ በእጅጉ አሳሳቢ የሆነ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ሕመም ውስጥ እንደገባች ዛሬ ባደረግነው ሕዝባዊ ስብሰባ አረጋግጠናል። ከአጋጠመን ብሔራዊ ፈተና በአሸናፊነት ለማለፍ እና በጋራ አገርን ለማዳን ሀገራዊ ጥሪ ማቅረብ እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ ደርሰናል። በመሆኑም፣ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከታች ለተጠቀሱ አራት አካላት ኢትዮጵያን የመታደግ አገራዊ ጥሪ አቅርበናል። ይህ ታሪካዊ አገራዊ ጥሪም ” የዲሲ አገራዊ ጥሪ” ተብሎ ስያሜ እንዲሰጠውም ተስማምተናል። ፩ኛ፡- ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቀረበ አገራዊ ጥሪ እኛ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የምንኖር ኢትዮጵያዊያን የአገራችን አንድነት የሚያስጨንቃቸው ዜጎች ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ባደረግነው ነጻ ውይይት ተገንዝበናል። በተለይም፣ በስራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት ዋና ይዘትና የገዢው ፓርቲ አጀንዳ በተግባር በታየበት በዚህ ወቅት፣ የሕዝቡ ስጋት ከባዶ የሚነሳ እንዳልሆነም ተረድተናል። በሌላ በኩል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የተረጋጋና ዋስትና ያለው ኑሮ ለማካሄድ ሰላም እንደናፈቀውና ሰላምን በእጅጉ እያሻ መሆኑን ተገንዝበናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የስልጣን ባለቤትነቱን በሕግና በስርዓት ካልተረከበ ሰላም እንደማይኖር፤ ሰላም ከሌለም ከገባንበት የድህነት አረንቋ መውጣት የዲ.ሲ አገራዊ ጥሪ እኛ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የምንኖር ኢትዮጵያዊያን፣ አገራችን ኢትዮጵያ ወደዚህ አሳሳቢ ደረጃ የሚያደርስ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ሕመም ውስጥ እንደገባች ዛሬ ባደረግነው ሕዝባዊ ስብሰባ አረጋግጠናል። ካጋጠመን እንዲህ አይነት ብሔራዊ ፈተና በአሸናፊነት ለማለፍና በጋራ አገርን ለማዳን ደግሞ ትብብርን የሚጠይቅ ወቅታዊ ጥሪ ማቅረብ እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ ደርሰናል። በመሆኑም በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከታች ለተጠቀሱ አራት አካላት ኢትዮጵያን የመታደግ አገራዊ ጥሪ አቅርበናል። ይህ ታሪካዊ አገራዊ ጥሪም ” ዲሲ ሪነሰንስ-2022″ ተብሎ ስያሜ እንዲሰጠውም ተስማምተናል። ፩ኛ፡- ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቀረበ አገራዊ ጥሪ እኛ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የምንኖር ኢትዮጵያዊያን የአገራችን አንድነት ከእንግዲህ ወዲያ ምን ዕድል እንደሚገጥመው ተስፋ በመቁረጥ ስሜት የሚጨነቁ ዜጎች ቁጥራቸው ቀላል እንዳልሆነ ባደረግነው ነጻ ውይይት ተገንዝበናል። በተለይም በስራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት ዋና ይዘትና የመንግስት አጀንዳ በለውጥ ስም የመገነጣጠል አጀንዳ ሆኖ በተግባር በታየበት ወቅት የሕዝቡ ስጋት ከባዶ የሚነሳ እንዳልሆነም ተረድተናል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሕዝብ የተረጋጋና ዋስትና ያለው ኑሮ ለማካሄድ ሰላም እንደናፈቀውና ሰላምን በእጅጉ እያሻ መሆኑን ተገንዝበናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የስልጣን ባለቤትነቱን በሕግና በስርዓት ካልተረከበ ሰላም እንደማይኖር፤ ሰላም ከሌለም ከገባንበት የድህነት አረንቋ መውጣት እንደማንችል ተረድተናል። ድህነቱ፣ የሰላም እጦቱ፣ የግፍ አገዛዙ፣ ዜጎችን ማዋከቡ ፣ ዘር ተኮር ጭፍጨፋው፤ የኢትዮጵያውያን ኩራትና ክብር መሟጠጡ፤ በመጨረሻም የተራዘመ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መገባቱ የአገራችንን ሕልውና እጅግ እንደተፈታተነው ተገንዝበናል። በመሆኑም፣ ኢትዮጵያውያን አገራችንን ከመፍረስ የመታደግም ሆነ የአገሪቱን የወደፊት ብሩህ ሕልም እውን ማድረግ የአንበሳው ድርሻ የእኛ ኢትዮጵያውያን መሆኑን ተገንዝበን በኃላፊነት መንፈስ መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል። ከአጋጠመን የፍትሕ እጦት፣ የእኩልነት መዛባት፣ በጨቋኞች አማካይነት ከሚደርስብን የኢኮኖሚ ባርነትና እንደ ሰው አለመቆጠር ነጻ መውጣት የምንችለው በራሳችን የነቃና የተደራጀ ተሳትፎ ብቻ ነው። ስለዚህም፣ መላው ኢትዮጵያውያን የተጋረጠብንን የአገር የመፍረስ አደጋ ለመቀልበስ ጊዜ የማይሰጠው ርብርብ እንድናደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በሌላ በኩል፣ ይህች የዓለም ኩራት የሆነች አገር በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በተከተለው የተሳሳተ የፓለቲካ አቅጣጫ ምክንያት የኢትዮጵያን ሕልውና አደጋ ላይ ጥሏል። ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ኢትዮጵያ ለሁለት መንትያ መርዞች ሰለባ መሆንዋ የችግሩ ዋና ሰንኮፍ ነበር ለማለት ይቻላል። እነዚህም፣ በሕገ መንግስት የተደገፈ የከፋፍለህ ግዛው ፓሊሲና ለኢትዮጵያ ችግር ተጨባጭነት የሌለው ርዕዮተ ዓለም ናቸው። እነዚህ ሰንኮፎች በጊዜውና በሰዓቱ ባለመነቀላቸው አገሪቱን ወደ እርስ በርስ ጦርነት፣ የዘር ተኮር ጭፍጨፋና የአገር ሕልውና አደጋ ጋርጠውባታል። የውጭ አገር መንግስታትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ድጋፍ የምትጠይቅበት ደረጃ ደርሳለች። በመሆኑም፣ በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ የተፈጠረው ጦርነት በዘላቂነት ለመፍታት፣ የዘር ተኮር ጭፍጨፋውን ለማስቀረትና አገራዊ አንድነቷን የጠበቀች ኢትዮጵያ እንድትኖር ሉዓላዊነታችንን በጠበቀ ሁኔታ አዎንታዊ ድጋፋችሁን እንድትሰጡን ለውጭ መንግስታትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጥሪያችንን እናቀርባለን። ፪ኛ፡- ለኢትዮጵያ መንግስት የቀረበ አገራዊ ጥሪ ባለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ጠላት የሆኑ አገዛዞች አንድ ካባ አውልቀው ሌላ ካባ በማጥለቅ በዘር፣ በጐሳ፣ በሃይማኖት እና በክልል የተከፋፈለች አገር እንድትኖር አድርገዋል። በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ጥላቻ፣ አለመተማመን፣ የጠላትነት አመለካከት እንዲኖር ወገባቸውን አስረው ሰርተዋል። ዛሬም እየሰሩ ነው። አሁን አዲሱን ካባ በብልጽግና ስም ያጠለቀውና በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ረገጣ አጠናክሮ በመቀጠል፤ ሕዝባዊ ቅራኔ፣ ቂምና ቁርሾ በመፍጠር፤ አገራችንን የማያባራ ጦርነት ውስጥ በመክተትና ዘር ተኮር ፍጅት በመፈጸም ራሱን ወደ አገር አፍራሽ ግብረ ኃይልነት ቀይሯል። በሌላ በኩል፣ የአገሪቱን ሁኔታዎች ስናገናዝባቸው ሥርዓቱ በኢትዮጵያ አንድነት፣ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊውና በፓለቲካው ፍልሚያ ተሸንፎአል። ለውጥ ተብሎ ብዙ የተዘመረለትም ጭምር በገዥው ቡድን አደናቃፊነት ሳይወለድ ተጨናግፏል። በመሆኑም፣ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የተሰባሰብን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መንግስት እየፈፀመ ካለው የአገር መፍረስ የተሳሳተ እንቅስቃሴና ዋነኛ ችግር ፈጣሪነት እንዲታቀብና የመፍትሔው አካል እንዲሆን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ፫ኛ፡ ለፓለቲካ ኃይሎች፣ ሲቪክ ማህበራት እና ማህበራዊ ተቋማት የቀረበ አገራዊ ጥሪ እኛ በዋሽንግተን ዲሲ የተሰባሰብን ኢትዮጵያውያን የምንወዳት ሀገራችንን ከመፍረስ አደጋ መከላከል የሚቻለው በፓለቲካ ኃይሎችና ሲቪክ ማህበራት መካከል የአእምሮና የመንፈስ ብቃትን በማሳደግ በውይይት፣ በንግግርና መደራደር ብቻ መሆኑን የፀና እምነት አለን። በእነዚህ ኃይሎች መካከል ውይይቱና ድርድሩ ፍሬያማ እንዲሆን ደግሞ፣ በቅን መንፈስ እና በቆራጥነት ከራስ የፓለቲካ ድርጅት ጥቅም ይልቅ የአራችንን ሕልውናና ሕዝቡን አስበልጦ መገኘት እንደሆነም እንገነዘባለን። በመሆኑም፣ በኢትዮጵያ የምትገኙ የፓለቲካ ኃይሎች፣ ሲቪክ ማህበራትና ማህበራዊ ተቋማት የኢትዮጵያ ሕዝብ የመጨረሻው የበላይ ባለስልጣን ስለሆነ ያለሕዝብ ፈቃድ ምንም ዘለቄታ የሚኖረው ውሳኔ ማድረግ እንደማይቻል አጥብቃችሁ እንድትገነዘቡ እንፈልጋለን። የሕዝቡ የእለት ተዕለት ጭንቀት የኢትዮጵያ ሕልውና አደጋ ላይ መውደቁ መሆኑን ተገንዝባችሁ፣ ለጊዜው የሚያለያዩአችሁን ጉዳዮች በይደር በማስቀመጥ አገራችን ኢትዮጵያ እያጋጠማት ካለው የመፍረስ አደጋ እንድትታደጓት ጥሪያችንን እናቀርባለን። ፬ኛ፡ ለውጭ መንግስታትና ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች የቀረበ ጥሪ ኢትዮጵያ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት አርአያ፤ ለአርነትና ለነጻነት ለሚሟሟቱ ሕዝቦች ሁሉ የኩራትና የተስፋ ምልክት የሆነች አገር መሆኗ ከማንም የተሰወረ አይደለም። በሌላ በኩል፣ ይህች የዓለም ኩራት የሆነች አገር በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በተከተለው የተሳሳተ የፓለቲካ አቅጣጫ ምክንያት የኢትዮጵያን ሕልውና አደጋ ላይ ጥሏል። ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ኢትዮጵያ ለሁለት መንትያ መርዞች ሰለባ መሆንዋ የችግሩ ዋና ሰንኮፍ ነበር ለማለት ይቻላል። እነዚህም፣ በሕገ መንግስት የተደገፈ የከፋፍለህ ግዛው ፓሊሲና ለኢትዮጵያ ችግር ተጨባጭነት የሌለው ርዕዮተ ዓለም ናቸው። እነዚህ ሰንኮፎች በጊዜውና በሰዓቱ ባለመነቀላቸው አገሪቱን ወደ እርስ በርስ ጦርነት፣ የዘር ተኮር ጭፍጨፋና የአገር ሕልውና አደጋ ጋርጠውባታል። የውጭ አገር መንግስታትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ድጋፍ የምትጠይቅበት ደረጃ ደርሳለች። በመሆኑም፣ በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ የተፈጠረው ጦርነት በዘላቂነት ለመፍታት፣ የዘር ተኮር ጭፍጨፋውን ለማስቀረትና አገራዊ አንድነቷን የጠበቀች ኢትዮጵያ እንድትኖር ሉዓላዊነታችንን በጠበቀ ሁኔታ አዎንታዊ ድጋፋችሁን እንድትሰጡን ለውጭ መንግስታትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጥሪያችንን እናቀርባለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply