የዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ ዓመታዊ የሚዲያ ሾውኬዝ ተከናወነ፡፡ዲኤስቲቪ በኤም ኔት ባለቤትነት በሚንቀሳቀሱት አቦል እና ማዲ አቦል በተሰኙ ቻነሎች እንዲሁም በሱፐርስፖርት ባለቤትነት በሱፐርስፖርት ል…

የዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ ዓመታዊ የሚዲያ ሾውኬዝ ተከናወነ፡፡

ዲኤስቲቪ በኤም ኔት ባለቤትነት በሚንቀሳቀሱት አቦል እና ማዲ አቦል በተሰኙ ቻነሎች እንዲሁም በሱፐርስፖርት ባለቤትነት በሱፐርስፖርት ልዩ 1 እና 2 ቻናሎች አማካኝነት ለኢትዮጵያ ተመልካቾች የተለያዩ መዝናኛ ፕሮግራሞችን በማቅረብ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ድርጅቱ በሐያት ሬጄንሲ ሆቴል ባዘጋጀው ፕሮግራም በመተላለፍ ላይ ያሉ እና በቀጣይ የሚጀመሩ አዳዲስ የመዝናኛ ፕሮግራሞቹን ያስተዋወቀ ሲሆን በዚህ መድረክ ላይ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ተጽዕኖፈጣሪ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዝግጅቱ ከ130 (አንድ መቶ ሰላሳ) በላይ የኢትዮጵያ ፕሮዳክሽን ኩባንያዎች ጋር የተለያዩ ስራዎችን በኤምኔት በኩል ተደራሽ መደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በዕለቱም ከ30 በላይ የሀገር ውስጥና ከ15 በላይ ዓለም አቀፍ የፊልም፣ መዝናኛና የስፖርት ይዘቶች በኤግዚቪዥን መልክና በአጫጭር ቪዲዮዎች ተቀንጭበው ቀርበዋል፡፡

የአፋፍ፣ የረቂቅ መንገድና የዳግማዊ ፕሮዲዩሰሮች በመድረኩ ላይ የአቦል ቴሌቪዥንን አስተዋጽኦ የመሰከሩ ሲሆን በርካታ የፊልም ባለሙያዎችም በዶክመንተሪ አስተያየታቸውን አጋርተዋል፡፡

የዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ ሬጉላቶሪ እና ኮርፖሬት ጉዳዮች ሃላፊ አቶ መታሰቢያ በላይነህ በመድረኩ ላይ እንዳሉት ዲኤስቲቪ ለደንበኞቹ በየጊዜው አዳዲስ የመዝናኛ ፕሮግራም እና ይዘቶችን እያቀረበ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ሲያቀርባቸው ከነበሩት የመዝናኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪ አዳዲስ ይዘቶችን እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ይቀርቡ ከነበሩት ይዘቶች በተጨማሪ አዳዲስ ፕሮግራሞች በአማርኛ እና በኦሮሚኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ይዘቶች ተዋውቀዋል፡፡

ዲኤስቲቪ አሁን ላይ በአቦል ቲቪ እና አቦል ዱካ ፕሮግራሙ አፋፍ፣ አጋሮቹ፣የዘመን ፈገግታ፣ አቦል ሚሊየነር፣ ዳግማዊ፣ ቁጭት፣ ጊዜ እና ሌሎችም መዝናኛዎች በማቅረብ ላይ ሲሆን የረቀቅ መንገድና ሀምዛ የተሰኙ አዳዲስ ይዘቶችን በቅርበ ይጀምራሉ ተብሏል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ

መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply