የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተዘጋጀውን የብሔር ብሔረሰቦች አውደ ርዕይ እየጎበኙ ነው

የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተዘጋጀውን የብሔር ብሔረሰቦች አውደ ርዕይ እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተዘጋጀውን የብሔር ብሔረሰቦች አውደ ርዕይ እየጎበኙ ነው።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት “ኑ ኢትዮጵያን በአንድ መድረክ እንያት” በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው አውደ ርዕይ የተለያዩ ዲፕሎማቶች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተገኝተው እየጎበኙት ነው።

በጉብኝቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ እጸገነት መንግስቱ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጨምሮ በርካታ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

15ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ የተከፈተው አውደ ርዕይ በበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተጎበኘ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

15ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን “እኩልነትና ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተዘጋጀውን የብሔር ብሔረሰቦች አውደ ርዕይ እየጎበኙ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply