የዳሸን ባንክ አቶ ዱላ መኮንንን በድጋሚ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበር አድርጎ መረጠ:: የዳሸን ባንክ ባለአክሲዮኖች ባካሄዱት 30ኛው መደበኛ ጉባኤ ባለፉት ሶስት ዓመታት ባንኩን በዳ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/spuPi5ONyjnNMYEdrqJ9MheoJMurQE0efHw_Jup75DNxGvgXUogvkWNrMOVGBXm4Oa2NwHZ0zQpF8V0YRWKKKxUjeoAO0jIRZTWw8vG5mEBkG7z-8SfOK_YARMU-xVkVx2XSHpOZTlWqeFYf1mRd-QjdhSR8m8oM4ZRlXHwOW7uu-lBYhBknVVPdPDzfxjHb2ndpJqfK7H2ZVqVT-hA8wsZZ0G4x6iyXsBlgOtBNENiagbZqRxU8qACTadQfbePqYOX_u-2RgMKJJ896VPe-I4NXHSuoI8l3QzX_wWNIhVixrGRS61lQQslLK2dYMrSQBTjEB-vjhs3tvowNyADajA.jpg

የዳሸን ባንክ አቶ ዱላ መኮንንን በድጋሚ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበር አድርጎ መረጠ::

የዳሸን ባንክ ባለአክሲዮኖች ባካሄዱት 30ኛው መደበኛ ጉባኤ ባለፉት ሶስት ዓመታት ባንኩን በዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበርነት ያገለገሉትን አቶ ዱላ መኮንንን በድጋሚ በዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበርነት መርጧል፡፡

ዳሽን ባንክ ለቀጣይ ሶስት አመታት ባንኩን በዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበርነት እንዲያገለግሉ በድጋሜ የመረጣቸው አቶ ዱላ መኮንን በአሁኑ ወቅት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕድን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

አዲስ የተመረጡት የቦርድ አባላት እና ባንኩን ላለፉት ሶስት ዓመታት ያገለገሉት የቦርድ አባላት የስራ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን ንዑስ ኮሚቴዎችንም ማዋቀሩን ባንኩ ለኢትዮ ኤፍኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ባንኩ አዲስ ለተመረጡት የቦርድ አባላት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴውን አስመልክቶ ገለፃ ማድረጉንም አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply