የዳኝነት ክፍያ ማሻሻያው ደንብ ሊስተካከል ይገባል ሲሉ የፌደራል የጠበቃዎች ማህበር አስታወቀ፡፡የጠበቃዎች ማህበር የዳኝነት ክፍያ ዋጋ ላይ የተደረገው ጭማሪ የኑሮ ውድነቱን ታሳቢ ያላደረገ…

የዳኝነት ክፍያ ማሻሻያው ደንብ ሊስተካከል ይገባል ሲሉ የፌደራል የጠበቃዎች ማህበር አስታወቀ፡፡

የጠበቃዎች ማህበር የዳኝነት ክፍያ ዋጋ ላይ የተደረገው ጭማሪ የኑሮ ውድነቱን ታሳቢ ያላደረገ ነው መባሉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያ መጨመር ፍርድ ቤቶች ለዜጎች ቀልጣፋ ፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው የዳኝነት አግልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑ ይነሳል፡፡

ይሁን እንጂ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ከጨመረ ከሳሽ ክሱን ወደ ፍርድ ቤት እንዳያመጣ እንቅፋት እንዳይሆን ስጋቶች እንዳሉባቸው ከጣብያችን ዚትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት የፌደራል ጠበቆች ማህበር ጠበቃና የህግ አማካሪ አቶ ታምራት ኪዳነማርያም ተናግረዋል፡፡

የፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ደንብ የወጣዉ ከ71 ዓመት በፊት በመሆኑ ለማሻሻያው ዋነኛ መነሻ መሆኑ ይገለፃል፡፡

የህግ አማካሪው እና ጠበቃ አቶ ታምራት “71 ዓመታትን የቆየው የዳኝነት ክፍያ ማሻሻያ መደረጉ መልካም ቢሆንም ጭማሪው ተጋኗል” ሲሉ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

ሌላው ሀሳባቸው የሰጡን ጠበቃና የህግ አማካሪ ተስፋዬ ዘውዴ ይህ ማሻሻያ ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል ታሳቢ ያደረገ አይደለም ይላሉ፡፡

እንደዚህ ዓይነት ጭማሪዎች ሲደረጉ በቅድሚያ የኑሮ ውድነቱን ከግምት ማስገባት እንዳለበት ያስረዳሉ፡፡

ዜጎች ፍትህ የማግኘት ሙሉ መብት አላቸው የሚሉት ጠበቃ ተስፋዬ በዚህ የዳኝነት ክፍያ መናር ዜጎች ከፍርድ ቤት እንዳይርቁ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ጣብያችን ያነጋገራቸው ፌደራል ጠቅላይ ፍረድ ቤት የምርምርና ህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሮን ደጎል በበኩላቸው 1945 የወጣን ደንም ማሻሻል ተገቢ ነበር ይላሉ፡፡

ምክንያቱም 71 ዓመታት ውስጥ በርካታ ጉዳዮች በመቀየራቸው ደንቡ መሻሻል እንደነበረበት ለጣብያችን ተገናግዋል፡፡

ዳይሬክተሩ የዳኝነት ክፍያ ደንብ ማሻሻያ በከፍተኛ ሁኔታ ጥናት ተደርጎበት ወቅቱን መሰረት ተደርጎ የተሰራ ማሻሻያ መሆኑ ገልፀዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ፍርድ ቤቶች ለዜጎች ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው የዳኝነት አግልግሎት እንዲሰጡ፣ ሕጉ ዘመኑ የደረሰበትን ነባራዊ እውነታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ደንቡን ለማሻሻል ውይይት አድርጓል፡፡

በአቤል ደጀኔ

መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply