የድምፃዊት ሃሌሉያ ተክለፃዲቅ አዲስ አልበም ነገ ይለቀቃል በቀድሞ ጃኖ ባንድ የምናዉቃት ተወዳጇ ድምፃዊት ሃሌሉያ ተክለፃዲቅ አዲስ የሰራችዉን “ተወዳጅ” የተሰኘ ሙሉ አልበም በነገው ዕለት ይ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/n8r1I7n30mqH4i65f_nlmhxYH1QEdXSi1d_35jIoANSRQpkfxuKK69VB7gL1dOXqxA00nOW-RGs_mjQip3MULUvIcAssnaxLRO3BVaglYOa60P8-VcIU_YZn7CkpvM4lfh4yGheCJ3Pm6QbUvuB7SXue_-BbjrdzoOUafl9rG4MVlTBADt_-DHOneL6aNhnhhl4g2z_cb0yhy0txLJmnEgTsTOYfGkOV9nd5oBGmhonqFmQDjcIunZoI7U9oISpHL0VkbWk60QD5wpOdnWuXkSsheK-tTf2PG6UJije0noKmCyhAo95dnGuAzvu_OJndUvuujYdhQmedl088v49CRA.jpg

የድምፃዊት ሃሌሉያ ተክለፃዲቅ አዲስ አልበም ነገ ይለቀቃል

በቀድሞ ጃኖ ባንድ የምናዉቃት ተወዳጇ ድምፃዊት ሃሌሉያ ተክለፃዲቅ አዲስ የሰራችዉን “ተወዳጅ” የተሰኘ ሙሉ አልበም በነገው ዕለት ይለቀቃል።

የአልበሙን መለቀቅ በማስመልከት ዛሬ መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘዉ ቦስተን ዴይ ስፖ ሚድታወን ክለብ  ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

ድምፃዊት ሃሌሉያ እንዲሁም በአልበሙ ላይ የተሳተፉት ዳዊት ተስፋዬ እና ኤንዲ ቤተ -ዜማ በጋራ በሰጡት ማብራርያ አልበሙ 13 ሙዚቃዎች የያዘ ሲሆን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሶስት ዓመት ያህል ፈጅቷል።

ነገ መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንተርኔት የሚለቀቀዉ ይኸው አልበም  በቅርብ ደግሞ በሲዲ እንደሚለቀቅ ገልፀዋል። በተጨማሪም በቅርቡ በሀገር ዉስጥ እና በዉጭ ሀገራት ኮንሰርት ለማዘጋጀት ዕቅድ እንዳላት ድምፃዊት ሃሌሉያና ባልደረቦቿ ተናግረዋል ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply