You are currently viewing #የድረሱልን_ጥሪ_ከዋግኽምራ_ሰቆጣ  ❻❼, ሺ ተፈናቃዮች! የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከ67,000 /ስልሳ ሰባት ሺ/  በላይ ተፈናቃይ በከፋ በችግር ውስጥ በመሆናቸው የድ…

#የድረሱልን_ጥሪ_ከዋግኽምራ_ሰቆጣ ❻❼, ሺ ተፈናቃዮች! የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከ67,000 /ስልሳ ሰባት ሺ/ በላይ ተፈናቃይ በከፋ በችግር ውስጥ በመሆናቸው የድ…

#የድረሱልን_ጥሪ_ከዋግኽምራ_ሰቆጣ ❻❼, ሺ ተፈናቃዮች! የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከ67,000 /ስልሳ ሰባት ሺ/ በላይ ተፈናቃይ በከፋ በችግር ውስጥ በመሆናቸው የድረሱልን ጥሪ ለህዝብ አድርሱልን ብለዋል። በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በአበርገሌ እና ጻግብጂ ወረዳዎች በጦርነቱ ምክንያት እስከ አሁን ድረስ በ2ቱ ወረዳወች የህወሓት ታጣቂወች በመኖራቸው እና ህዝቡ ላይ የከፋ ችግር እያደረሱ በመሆኑ ከቦታው ተፈናቅለው በሰቆጣ ከተማ በሶስት መጠለያ ጣብያዎች መኖር ከጀመሩ ሰነባብተዋል ተፈናቃዮቹ ከ2 ወር እስከ 2 አመታት ቆይታ ያስቆጠሩ ናቸው። በነዚህ ጊዚያ ውስጥ በሁለተኛው መፈናቀል ሲመጣ ከነበረው ድጋፍ ውጭ በ3ኛ ዙር ተፈናቅለን ከመጣን ቡኋላ ድጋፍም ሆነ እርዳታ አልደረሰንም ይላሉ በመጠለያ ጣብያ ያሉ ተፈናቃዮች። ከአበርገሌ ወረዳ ተፈናቅለው የመጡት ወይዘሮ እስከዳር ገብሬ ከመጣን አንድ አመት አስቆጥረናል። ቤታችንና ንብረታችን ትተን ባዶ እጃችን ነው የመጣነው፤ እዚህ ከመጣን በኋላም ምንም የረባ ነገር አላገኘንም፤ አሁን የሚበላ የለንም፤ ልብስም የለንም ባዶ ነው ያለነው፤ ምኝታም የለንም ስሚንቶ ላይ ነው የምንተኛው ይላሉ። ሌላኛዋ ተፈናቃይ ወይዘሮ ብርቱካን ወረታ ናቸው። ከመጣን አንድ አመት ሊሞላን ነው ግን የሚመጣው ድጋፍ ለሁሉ ተደራሽ አይሆንም። በተለይ አረጋውያን ምንም እያገኙ ስላልሆነ በጣም ተጎድተዋል፤ ተርበዋል፤ ከቀይ መስቀል ውጭ ሌላ እርዳታ የሰጠን የለም። ልብስም መኝታም የለንም ብለዋል። አቶ ጻዲቅ አክለውም እዚህ በርሀብ ምክንያት እንደወጣን ሙተን ከምንቀር እዚያው አከባቢያችን ሄደን እንሙት። ውሃ እንኳ ቀድቶ የሚሰጠኝ የለኝም ሲሉ ተናግረዋል። የመጠለያ ካምፑ አስተባባሪ አቶ ፀሀየ ሙላው በበኩላቸው፣ ከአንድ አመት በላይ ሆኖናል። ህይወታችን ማለቱ ጥሩ ነው፤ ግን በችግር ውስጥ ነው እየኖርን ያለነው፤ በጣም ተጎድተናል። በተለይ ምንም ሰርተው ለማይበሉ አቅመ ደካማ አረጋውያን ድጋፍ አይደረግም። አሁን ላይ አረጋውያን በጣም ችግር ውስጥ ነው ያሉት ብለዋል። የፃግብጅ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቸኮለ አበበ በበኩላቸው የሰላም ስምምነቱን የምንደግፈው ቢሆንም ህዝባችን ወደ አካባቢው እንዲመለስ ባለመደረጉ ለርሀብ ተዳርጓል ብለዋል። ከነሐሴ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተፈናቅሎ ያለውም ሆነ አገር ቤት ያለው ህዝባችን ለርሃብ፣ እንግልት፣ እርዛትና ችግር እንዲሁም ለከፍተኛ ሞራላዊ ችግር ተጋልጧል። እዚያ የቀሩት ወገኖቻችን በተለይ ወላዶች፣ህፃናትና አረጋውያን በህክምና እጦት እየተሰቃዩና እየሞቱ ነው፤ ከታመመ ተስፋ መቁረጥ ነው አይድንም ብለዋል። ከሶስተኛው ጦርነት በኋላ ተፈናቃይ ህዝባችን እንዳለ እየታወቀ መንግስት እረስቶናል፤ እረጅ ድርጅቶችም ድጋፋቸውን አቁመዋል ሲሉ ጨምረው የተናገሩት አቶ ቸኮለ በዚህ የተነሳም ህዝባችን ለከፍተኛ እርሃብና ጥም እየተጋለጠ ስላለ መንግስት በአስቸኳይ ወደ አካባቢያችን እንዲመልስልን እንፈልጋለን። ህዝባችን ከቦታው ሂዶ ህወቱን መምራት እርሻውን ማረስና ልማቱን ማልማት አለበት ነው ያሉት። መንግሰት ለትግራይ ህዝብ ያልተቆጠበ እርዳታ እየሰጠ ያለው ጥሩ ቢሆንም ለእኛ ህዝብ በተለይ አሁንም ድረስ ተፈናቅሎ ለሚገኘው የፃግብጅና አበርገሌ ህዝብ ለምን እንደማይሰጥ አልገባንም። ችግሩን ለክልሉ መንግስት በተደጋጋሚ ብናስታውቅም እስካሁን ምላሽ አላገኘንም፤ ሲሉም አቶ ቸኮለ ያላቸውን ቅሬታ ተናግረዋል። የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ተጠሪ ጽ/ቤት ተወካይ ወይዘሮ ዝናሽ ወርቁ እንደተናገሩት፣ ከኢመርጀንሲ እና ቀይ መስቀል ከሰጠው እርዳታ ውጭ ድጋፍ አልተደረገም። መንግስታዊ ካልሆኑ በጎ አድራጊ ድርጅቶች የሚሰጠው ድጋፍም ከነሐሴ ማለትም ከሶስተኛው ዙር ጦርነት በኋላ ቀንሷል። ከ67 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ባለበት ሁኔታ መንግስት ወደ መልሶ ማቋቋም ፊቱን ስላዞረ ተፈናቃዮች እየታዩ አይደለም ብለዋል። ሁለት ወረዳ ሙሉ በሙሉ በጠላት ቁጥጥር ስር ነው ያለው ይህ ደግሞ ቀየውን ጥሎ፣ ቤቱን ዘግቶ የመጣ በመሆኑ ድጋፉም ሆነ እርዳታው መቀጠል አለበት ሲሉም ወ.ሮ ዝናሽ አክለው ተናግርዋል። እንደ ብሔረሰብ አስተዳደርም ይህንን አስመልክቶ ውይይት አድርገናል ይህም ለትግራይ ክልል የሚላከውን ያህል ለምን ለእኛስ አይመጣም የሚለውን ተነጋግረናል። በዚህም ቢያንስ በእነሱ ቁጥጥር ስር ባሉ ወረዳዎች የሚኖሩ ወገኖቻችን እንኳ እየተረዱ አይደለም። በተለይ አበርገሌና ፃግብጅ ከሁለት አመት በላይ በጠላት ቀጠና ውስጥ በመሆኑ ችግሩ በቀላል የሚታይ አይደለም፤ ከርሀቡ ባሻገር የስነ-ልቡና ችግርም እየደረሳባቸው ስለሆነ ትኩረት መደረግ አለብት ሲሉ ገልጸዋል ወ.ሮ ዝናሽ። ኮረም፣ወፍላ፣ዛታ፣ አላማጣ፣ዝቋላና ፀመራ ወረዳዎች ከጦርነቱ ነፃ ስለወጡ 29 ሺህ 262 ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው የተመለሱ ሲሆን በአጠቃላይ እንደ ብሔረሰብ አስተዳደር አሁን ያለው የተፈናቃይ ብዛት 67 ሺህ 961 እንደሚሆንና ከእዚህ ውስጥ 4 ሺህ 662 የሚሆኑት አዲስ የመጡ ተፈናቃዮች እንደሆኑ ከጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክት ያደረሰን ቤተ አምሃራ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply