የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ባለፉት ስድስት ወራት ከ596 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ባለፉት ስድስት ወራት ከ596 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት ግማሽ ዓመት ከ596 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በስድስት ወራት 640 ሚሊየን 707 ሺህ 116 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ፥ 596 ሚሊየን 444 ሺህ 660 ብር መሰብሰብ መቻሉን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አብዱሠላም መሐመድ ተናግረዋል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር ባለፉት ስድስት ወራት የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ15 ሚሊየን 352 ሺህ 200 ብር ብልጫ እንዳለውም ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

ለግብር ከፋዩ ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መሰራቱ፣ ደረሰኝን የመጠየቅ ልማድ በማደጉና ህገወጥ ንግድን የመከላከልና ህግ የማስከበር ስራ መሰራቱ ለተገኘው ገቢ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውም ተጠቅሷል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ባለፉት ስድስት ወራት ከ596 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply