የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከነገ የሚጀምር ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ የሰዓት ገደብ አስተላለፈ

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከነገ የሚጀምር ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ የሰዓት ገደብ አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከነገ የሚጀምር ከከባድ ተሽከርካሪዎች የከተማ ውስጥ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የሰዓት ገደብ ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ የሰዓት ገደቡን ያሳለፈው በአስተዳደሩ እየተከሰተ ካለው የትራፊክ መጨናነቅና በዚህም ሳቢያ እየተፈጠረ ያለውን የመንገዶች መዘጋትና መጉላላት ለመቀነስና ለማስቀረት አስቦ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

ገደቡ ከነገ ጀምሮ ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስን ያግዳል ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ይሁን በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ የፈቀደው ከምሽት 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ብቻ መሆኑን ከድሬ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

The post የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከነገ የሚጀምር ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ የሰዓት ገደብ አስተላለፈ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply