የድሬዳዋ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣ በቂ የሆነ የመጠጥ ውሃ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ አልተቻለም አለ፡፡የድሬደዋ የውሃና ፈሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መሃመድ ሙሳ ከጣቢያችን ጋር…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/tDPAlwwg5FLkpfas6XRVWUasS0Cc0wFJdeQR373nbXObW7xeIqRPr59MDSoC1LV9OxqvV5jsEZvRpRlDDEBWVdHJnx1JtfKd1ItOKemo6RkIm3We4QSIszComD7GwMuchdUePMZNGWvvMgm_VJAgG3s8dfq1s1JbUkAcWHsXW16aMECQTzKeCvroPYjyX0DX1ulwekOtMDokAACYofTucTSqnq8kQL6kwu57vDYBQWDTYr2pNIx9ZM79qh3cI-lBGUasJnYxQr-T1qzZxM8bDWzfrOls9NZYUp3k4z6JqlVofHfXz65OzFcLSSfRpLjbTxD4fe8IF5e7kWOJqlPOcA.jpg

የድሬዳዋ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣ በቂ የሆነ የመጠጥ ውሃ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ አልተቻለም አለ፡፡

የድሬደዋ የውሃና ፈሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መሃመድ ሙሳ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ የማህበረሰቡን የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ፍላጎት ማመጣጠን አለመቻሉን ተናግረዋል።

አሁን ያለው የውሃ አቅርቦት የከተማዋን እድገት አይመጥንም ያሉት አቶ መሃመድ ለዚህም እያደገ በመጣው ከተማ ልክ መሰረተልማቱን እኩል ማስኬድ ባለመቻሉ ነው ብለዋል።

አሁናዊ የመጠጥ ውሃ እጥረትን ለመቅረፍ በባለስልጣኑ ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደስራ ቢገባም አሁን ካለው የመጠጥ ውሃ ፍላጎት አንፃር በቂ አይደለም ነው ያሉት።

የበጀት እጥረት ፣የውሃው ጨዋማ መሆን ፣ በየጊዜው የውሃ ቱቦው መደፈንና መቆራረጥ፣ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳለም ሰምተናል።

በልዑል ወልዴ

የካቲት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply