የድጋፍ ሰልፎች በወሎ

https://gdb.voanews.com/E0857AA6-6016-43B4-A6A6-2DB81F8D587B_cx8_cy0_cw72_w800_h450.jpg

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይንና የለውጥ አመራሩን የሚደግፉ ትእይንተ ህዝቦች በአማራ ክልል ደሴ፣ ደቡብ ወሎና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ተካሂደዋል፡፡

ሰልፈኞቹ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግድያና መፈናቀል እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡

መንግሥት በመተከልና በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ መመከትና መከላከል አለበት፣ በሃገር ጥፋት ላይ ተሰማርቶ የነበረው የህውሓት ታጣቂ ቡድን ላይ የተወሰደውን ወታደራዊ ርምጃናየተገኘውን ድል እንደግፋለን የሚሉና በርካታ መፈክሮችን ያነገቡ ሰልፈኞች በሆጤ ስታዲየም ተገኝተዋል፡፡

የደሴ ከተማ ከንቲባ አበበ ገ/መስቀል ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ህዝብን ከህዝብ የሚነጥሉ የሃሰት ትርክቶች ሆን ተብሎ እንዲስፋፋ በመደረጉ በተለይ የአማራ ተወላጆች ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ እንዲፈናቀሉና የህይወት መስዋእትነት እንዲከፍሉ መደረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply