የዶንጋ ብሄረሰብ ከፍተኛ የመብት ጥሰት እየተፈፀመበት ነዉ ሲል የዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ፡፡ፓርቲዉ በዶንጋ ብሄረሰብ ላይ የመብት ረገጣና ጥሰት እየተፈጸመበት መሆ…

የዶንጋ ብሄረሰብ ከፍተኛ የመብት ጥሰት እየተፈፀመበት ነዉ ሲል የዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ፡፡

ፓርቲዉ በዶንጋ ብሄረሰብ ላይ የመብት ረገጣና ጥሰት እየተፈጸመበት መሆኑን በዛሬው እለት በሰጠዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡

ህዝቡ በህገ-መንግስቱ የተፈቀደዉን የእራስን በራስ የማስተዳደርና የመልማት መብቱን ሲያነሳ ለአፈና እና እስር እየተዳረገ መሆኑን አንስቷል፡፡

በሰላማዊ መንገድ በህግ አግባብ በልዩ ወረዳ የመደራጀት ህገ-መንግስታዊ መብቱን ህዝቡ ቢጠይቅም፤የቀድሞ የከምባታ ጠምባሮ ዞን የብሄረሰቡን ህዝቦች እያንገለታ ነዉ ብሏል ፓርቲዉ በመግለጫዉ፡፡

የሀደሮ ከተማ አስተዳደርም በዶንጋ ህዝብ ላይ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ በመግለጫዉ አንስቷል፡፡
የብሄረሰቡ ተወላጅ ተማሪዎችም በነጻነት እንዳይማሩ እየተደረገ እንደሆነም ገልጧል፡፡

በተጨማሪም የዶንጋ ብሄረሰብ የባህል አካል የሆኑ የቱሪስት መስህቦችን ለመንጠቅ በዞኑ እንስቀሳሴ ተጀምሯል ሲል ከሷል፡፡

በመሆኑም ይህ አይነቱ ተግባር ሉአላዊ ብሄረሰብ ባህላዊ እሴቶችን የመዝረፍ ህገ-ወጥ ተግባር በመሆኑ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልና የፌደራሉ መንግስት እንዲያስቆሙ ፓርቲዉ ጥሪዉን አቅርቧል፡፡

የዶንጋ ወጣቶች የያሆዴ መስቀል በዓልን ለማክበር ወደ ሃድያ ባቀኑበት ወቅት ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቁ ወጣቶች በፀጥታ ሃይሎች መታሰራቸዉና የት እንዳሉ እንኳን መረጃ እንደሌለዉ ፓርቲዉ አስታዉቋል፡፡
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ይህን ወንጀል በሚፈጽሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድም የዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ጠይቋል፡፡

በአባቱ መረቀ
መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply