የዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥ የጎሳ ፍለጋ እና የፖለቲካ ተፅእኖ እየተስተዋለበት ነዉ ተባለ።የዩንቨርስቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥ ግልፅ መመሪያ እንዲዘጋጅለት ተጠይቋል። በልዩ ልዩ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Fr-u2LMlLo_NSKbbNVKuswN2Lt7CBWV5l_QCm0FtUkIt5nqHNCAt1ZxjE-ZtxpP0bUiYhZsalib5QQJyKWDWuRBPLAkZj4iM01EmladsiZm3u_Ke2g4cgxon_UtC5YYkKruKQx4EKL0jmZOF1rdWFDOegEY5Zj9BO_7ZVmE0GhV6a7HKxe0JLO3bADq-qD-q0vQ2SFcnacVr4I25PShPBRmJASEOyCeuHQK7F7rmekZJrgEEEQHItWYG-7sekF69Oyf-xr51bY_zinbAljMeW6teNYHEjS3Z-abotf7KMu0cgLLfIGg06OuDQTUwAqzUL-AYCXDsCvTtuZKkfXR6FQ.jpg

የዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥ የጎሳ ፍለጋ እና የፖለቲካ ተፅእኖ እየተስተዋለበት ነዉ ተባለ።

የዩንቨርስቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥ ግልፅ መመሪያ እንዲዘጋጅለት ተጠይቋል።

በልዩ ልዩ አስተዋጽኦ እና የስራ አበርክቶ ላላቸዉ ግለሰቦች የዩንቨርስቲ ቆይታ ሳይጠበቅባቸዉ ለ እዉቅና የሚሰጠዉ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ከጥቂት አመታት ወዲህ የጎሳ ፍለጋ እና የፖለቲካ ተፅእኖ እየተስተዋለበት ነዉ ተብሏል።

በመሆኑም ግልፅ የሆነ መመሪያ እና ሂደት መዘጋጀት እንዳለበት ተጠቁሟል።

ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥን በሚመለከት መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ/ም ባደረገዉ ዉይይት ነዉ።

በዉይይቱ ገለፃ ያደረጉት ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ ይህ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አላማ ክብር ሰጥቶ ክብር ለማግኘት የሚደረግ ስርአት ነዉ ያሉ ሲሆን ሆኖም እየታዩበት ያሉ ችግሮች የቦታ ተወላጅን የመፈለግ እና የቦርድ አባላቱ የፓለቲካ ባለስልጣናት በመሆናቸዉ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሽልማት እንጂ ለመጠሪያነት የማያገለግል እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በመገናኛ ብዙሃን ላይ የክብር ዶክትሬት ዲግሪን እንደ ቅጥያ ስም አድርጓ ማስተዋወቅ ስህተት ነዉ ተብሏል ።

ለዚህም የጠራ መረጃ እንደሚያስፈልግ እና መመሪያዉም ይሄን ሊያካትት እንደሚገባው በአፅንኦት ተገልፃል።

የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ዋጋዉን እንዳያጣ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል የተባለ ሲሆን በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ኘሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በዚህ አመት የሚጠናቀቅ መመሪያ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።

በቁምነገር አየለ

መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply