የጀበና ቡና ሻጯ የ3 ሚሊዮን ብር ሎተሪ አሸነፈች።

ግለሰቧ ከተደጋጋሚ የሎተሪ ሙከራ በኋላ ነው ባለእድለኛ መሆን የቻለችው።

የአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ለምለም ሽፈራው የጀበና ቡና በመሸጥ የምትተዳደር ሲሆን ከተደጋጋሚ የሎተሪ ሙከራ በኋላ 3ሚሊዮን ብር በእጇ ማስገባቷ ተገልጿል።

የሎተሪ አዟሪው ባለእድለኛዋ ቡና በምታፈላበት ቦታ ድረስ በመሄድ የልዩ ሎተሪው ቲኬት እንደሸጠላት ነው የተናገረችው።

ዕድል እስከ ስራ ቦታዋ ድረስ የተከተላት ይህቺ ግለሰብ በገዛችው ሙሉ ዕጣ ሎተሪ የ3ሚሊየን ብር ዕድለኛ ልትሆን ችላለች።

ባለእድለኛዋ ወ/ሮ ለምለም የሁለት ልጆች እናት ሲትሆን በደረሳት ሶስት ሚሊዮን ብር ለልጆቼ የሚያስፈልጋቸውን አሟላበታለሁ ብላለች።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply