የጀውሃ አካባቢው ግጭት ውሎ

https://gdb.voanews.com/06a20000-0aff-0242-7a75-08daff13a0f3_tv_w800_h450.jpg

ባለፈው ቅዳሜ ጥር 13 በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጀውሃ አካባቢ በተቀሰቀሰው ግጭት ከሰሜን ሸዋም ከኦሮሞ ብሔረሰብ ዞንም ብዙ ህይወት መጥፋቱና ሰፊ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

የክልሉ መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ‘ፀረ ሰላም’ ሲል የጠራቸው ታጣቂዎች ‘በክልሉ ልዩ ኃይልና ፌደራል ፖሊስ ላይ ጥቃት ፈፅመው ጉዳት አድርሰዋል’ ብሏል።

መግለጫው ጥቃት አድራሾቹ በሰሜን ሸዋ ዞንና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ውስጥ በሚኖሩ “ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን” አመልክቷል።

በከባድ መሳሪያ የታገዘ ነው በተባለው ጥቃት የንብረት ጉዳትም መድረሱን ከአካባቢዎቹ የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply