You are currently viewing የጀግናው ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ ከበደ ስርዓተ ቀብር በአምባስል ወረዳ 03 ቀበሌ በሮቢት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተፈፀመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      ጥር 8 ቀን 2015 ዓ/ም…

የጀግናው ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ ከበደ ስርዓተ ቀብር በአምባስል ወረዳ 03 ቀበሌ በሮቢት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተፈፀመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ/ም…

የጀግናው ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ ከበደ ስርዓተ ቀብር በአምባስል ወረዳ 03 ቀበሌ በሮቢት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተፈፀመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የጀግናው ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ ከበደ የቀብር ስርዓተ ቀብር በአምባስል ወረዳ 03 ቀበሌ በሮቢት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በወታደራዊ ክብር በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ በ03 ቀበሌ ሮቢት ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች፣ የአምባስል ወረዳ አመራሮችና የጸጥታ ኃይሎች፣የሃይማኖት አባቶችእና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ነው መፈፀሙ ተገልጧል። ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ ከበደ ጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም በደረሰባቸው በድንገተኛ ህመም ምክንያት በ43 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል። ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ ከበደ አጭር የህይወት ታሪክ:_ ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ ከበደ ከአባታቸው ከዓለቃ ከበደ ማሞ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ያምሮት ረዳ በቀድሞው የትግራይ ክፍለ ሐገር በአዲግራት ከተማ ሐምሌ 3 ቀን 1972 ዓ.ም ተወለዱ። እድሜያቸውለትምህርት ሲደርስም ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በማይጨው ከተማ ተከታትለዋል። ወላጆቻቸው ወደ ቀድሞ የትውልድ ቦታቸው ወደ አምባሰል ወረዳ 03 ቀበሌ ሮቢት ሲመለሱም ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በውጫሌ ትምህርት ቤት እንዲሁም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ደግሞ በሃይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምረዋል። በ1990 ዓ.ም ሻዓቢያ የሐገራችንን ሉዓላዊነት ሲዳፈር የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው በብር ሸለቆ መሰረታዊ የውትድርና ማሰልጠኛ ማዕከል በመግባት የውትድርና ስልጠናቸውን ተከታትለዋል። የውትድርና ብቃትን ከተላበሱ በኋላም በተለያዩ የጦር ክፍሎች ከተራ ተዋጊነት እስከ ከፍተኛ አዋጊነት በ20ኛ ፣በ15ኛ ፣በ18ኛ ፣በ23ኛና በ76ኛ ክፍለ ጦሮች በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ላይ ተሰልፈዋል። በተለይም የሰሜን ዕዝ በህወሓት ታጣቂዎች ጥቃት ከደረሰበት በኋላ በትግራይ ክልል በተደረገ የህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ተሰልፈው ግዳጃቸውን በብቃት ተወጥተዋል። በተጨማሪም ህወሓት በአማራና በአፋር ክልሎች ወረራ በፈፀመበት ወቅት ወረራውን ለመቀልበስ በተደረገው ትግል በአፋር ክልል ጭፍራ ግንባር የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው ህክምናቸውን ከተከታትሉ በኋላ ወደ ጦር ክፍላቸው ተመልሰው ግዳጃቸውን ተወጥተዋል። በ2015 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሽሬ ግንባር አዲሐገራይ በተባለ ቦታ ቆስለው በዝዋይ ህክምና ማዕከል ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ወደ ክፍላቸው በመመለስ ግዳጃቸውን ለመወጣት ቤተሰባቸውን ጠይቀው ለመሄድ አምባሰል ወረዳ 03 ቀበሌ ሮቢት መጥተው ሳለ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ጥር 4/2015 ዓ.ም በተወለዱ 43 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ ከበደ ለ25 ዓመት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባል ሆነው ሐገራቸውን በቅንነት፣በታታሪነትና በታማኝነት አገልግለዋል። በተጨማሪም ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ ከሐገር ውስጥ ግዳጅ አልፈው ሐገራቸውና ህዝባቸው የጣለባቸውን የውጭ ሐገር የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ተቀብለው በሱዳን ዳርፉር ግዳጃቸውን በመወጣት በክብር ወደ ሐገራቸው የተመለሱ ጀግና መኮነን ነበሩ። ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ አኩሪ ገድል በመፈፀም ጀግንነትንና ታታሪነትን አስተምረዋል። ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም የትግል ታሪካቸው ለዘላለም የማይረሳ ታሪክ አስቀምጠው አልፈዋል። ሌተናል ኮሎኔል ታደሰ ከበደ ባለትዳርና የሁለት ወንዶች እና ሦስት ሴት ልጆች አባት ነበሩ። አምባሰል ወረዳ ኮሙኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply