የጀግናው ፋኖ ሽአለቃ ዘማች ሞላ መታሰቢያ በዛሬው እለት በባህርዳር ከተማ በትግል አጋሮቹ ታስቦ ዋለ። አሻራ ሚዲያ ጥር 02/05/2014 ዓ.ም ጀግናው ፋኖ ሽአለቃ ዘማች ከልጅነቱ ጀምሮ…

የጀግናው ፋኖ ሽአለቃ ዘማች ሞላ መታሰቢያ በዛሬው እለት በባህርዳር ከተማ በትግል አጋሮቹ ታስቦ ዋለ። አሻራ ሚዲያ ጥር 02/05/2014 ዓ.ም ጀግናው ፋኖ ሽአለቃ ዘማች ከልጅነቱ ጀምሮ ወያኔን የታገለ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ነዉ በማዕከላዊ ታስሮም ብዙ እንግልት እና ግፍ ደርሶበታል ፡፡ ፋኖ ሽአለቃ ዘማች ሞላ ከአስር ቤት እንደወጣም ከብ/ጄኔራል አሳምነዉ ጥጌ ከአስቻለዉ ደሴ እነዲሁም ከሌሎች የትግል አጋሮቹ ጋር በመሆን ፋኖን በማደራጀትና በማሰልጠን ታላቅ ስራ የሰራ ነበር ፡፡ ፋኖ ሽአለቃ ዘማች በጎንደር በጠለምት በአጣየ በላሊበላ በዳዉንት በደብረዘቢጥ በሰቆጣ በገረገራ አርቢት በላስታ ኮረብቶች እና ግንባሮች ጠላት የቃጣውን ጥቃት በመመከት የተለያዩ የጀግንነት ጀብድን የፈፀመ ጀግና ነበር። ፋኖ ሽአለቃ ዘማች በዳዉንት ግንባር ወደፊት ጠላትን እንደ ቅጠል እያረገፈው ከባድ ተጋድሎን ፈፅሞ ለአማራ ህዝብ ነፃነት ለእናት ሀገሩ በክብር እና በፅናት ተሰውቷል። ታዲያ የጀግናው ፋኖ ሽአለቃ ዘማች ሞላ መታሰቢያ በዛሬው እለት በባህርዳር ከተማ የትግል አጋሮቹ በተገኙበት ታስቦ ዉሏል። ፋኖ ሽአለቃ ዘማች የሦስት ልጆች አባት ሲሆን አሁን ላይ ባለቤቱ ምንም አይነት ድጋፍ ስላልተደረገላት እነዲሁም የሚያግዛት አካል ባለመኖሩ በችግር ላይ እንደምተገኝ አሻራ ሚዲያ ከቦታዉ በመገኘት ተዝቧል ባለቤቱ ምንቴ አለምነዉ ለአሻራ ሚዲያ እነደገለፀችዉ አሁን ላይ ምንም ነገር የለኝም የሶስት ልጆች እናት ነኝ የምኖረዉ ተከራይቸ ነዉ ሶስተኛ ልጀን ከወለድኩ ጋና 30 ቀኔ ነዉ በጣም ችግር ዉስጥ እገኛለሁ ያለች ሲሆን የሚመለከተዉ ሁሉ እነዲያግዛት ጠይቃለች፡፡ የመንግስት አካላት ለፋኖ ቤተሰቦች እንኳን ለሞተ ለቆሰለም እንደሚያግዝ ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ያሸነፈ ሲመስለዉ እንኳን ሊያግዝ ይቅር እና እኛን ማሳደድ ነዉ የያዘዉ ሲሉ የትግል አጋሮቹ በምሬት ይናገራሉ አክለዉም ለተሰዉ የፋኖ ቤቴሰቦች ሁሉም ሊያግዝ እና ሊረዳ እነደሚገባ ገልፀዋል ፡፡ ለእኛ ነፃነት ራሱን አሳልፎ ሲሰጠን እኛ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ የእሱ የሆኑትን ልጆቹን የማሳደግ መንከባከብ ህዝባዊ ኀላፊነት አለብን። ፋኖ ሽአለቃ ዘማች ቤተሰቦች መርዳት ለምትፈልጉ የባለቤቱ ስልክ ቁጥር +250975020826 ማግኘት ትችላላቹህ ከፋኖ ሽአለቃ ዘማች ቤተሰቦች እና ትግል አጋሮቹ ያደረግነዉን ቆይታ በዩቱብ ቻናላችን የምናቀርብ ይሆናል ፡፡ ዘጋቢ ጌትነት ያለዉ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply