You are currently viewing የጀግኖቹ እሸቴ ሞገስና ይታገስ እሸቴ የቀብር ስነ ስርዓት ጥር 1 ቀን 2014 በሸዋሮቢት ስለሚካሄድ ተገኝታችሁ የአስከሬን ሽኝቱ አካል እንድትሆኑ ሲሉ ቤተሰቦችና ጊዜያዊ አስተባባሪዎች ጥሪ…

የጀግኖቹ እሸቴ ሞገስና ይታገስ እሸቴ የቀብር ስነ ስርዓት ጥር 1 ቀን 2014 በሸዋሮቢት ስለሚካሄድ ተገኝታችሁ የአስከሬን ሽኝቱ አካል እንድትሆኑ ሲሉ ቤተሰቦችና ጊዜያዊ አስተባባሪዎች ጥሪ…

የጀግኖቹ እሸቴ ሞገስና ይታገስ እሸቴ የቀብር ስነ ስርዓት ጥር 1 ቀን 2014 በሸዋሮቢት ስለሚካሄድ ተገኝታችሁ የአስከሬን ሽኝቱ አካል እንድትሆኑ ሲሉ ቤተሰቦችና ጊዜያዊ አስተባባሪዎች ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጀግኖቹ እሸቴ ሞገስና ይታገስ እሸቴ የአስከሬን ሽኝት ጥር 1 ቀን 2014 የሚከናወን መሆኑን ቤተሰብ እና ጊዜያዊ አስተባባሪዎች አስታውቋል። የጀግኖቹ የአስከሬን ሽኝት ከሳላይሽ ወደ ሸዋሮቢት መኖሪያ ቤታቸውና ከዛም ወደ ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ዘመድ፣ አድናቂዎችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት ለማከናወን እቅድ ተይዟል። ጀግኖቹ አባትና ልጅ እሸቴ ሞገስ እና ይታገስ እሸቴ ሳላይሽ ላይ 9 አሸባሪዎችንና ወራሪዎችን ገድለው ከመሰዋታቸው ባሻገር አቶ እሸቴ ሞገስ የሰሩትን ጀብድ ‘መዝግብ’ እያሉ ለትውልድ ማስቀረታቸው የብዙዎችን ቀልብ ስቧል፤ አስመስግኗቸዋል፤ ከፍ ብሎም እንዲነገርላቸው አድርጓል፡፡ አቶ እሸቴ ሞገስ በ56 ዓመታቸው፣ ልጃቸው ይታገስ እሸቴ ደግሞ በ31 ዓመታቸው ነው በደም እና በአጥንታቸው ለትውልድ የሚበጅ የማይሞት ታሪክ ሰርተው በመስዋዕትነት ያለፉት። ለእነዚህ በክብር ለወደቁት ወንድሞቻችሁና ለቤተስቦቻቸው በተለያየ መንገድ ሀዘናችሁን ለገለጻችሁልን ከሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ሆናችሁ እንዲሁም በቤት በመገኘትም ላጽናናችሁንና ድጋፍ ላደረጋቺሁልን ውድ ኢትዮጵያውያን ከፍ ያለ ምሥጋናችንን ይድረሳችሁ ብለዋል ቤተሰቦቻቸውና ጊዜያዊ አስተባባሪዎች። ጥር 1 2014 ዓ/ም በሚከናወነው የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ ተገኝታችሁ ለጀግኖቹ ደማቅ አሸኛኘት እንድናደርግላቸው ጥሪ እናስተላልፋለን ብለዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃ ለምትፈልጉ በሚከተሉት ቤተሰቦቻቸውና ጊዜያዊ አስተባባሪዎች ስልክ ቁጥሮች ልታገኙን ትችላላችሁ፡- ዶ/ር ይተብቱ ሞገስ – ስ/ቁ. 0912865584 ወ/ሮ ኤደን አማረ – ስ/ቁ. 0911393646 አቶ እዮብ ጠንክር – ስ/ቁ. 0912159425 አቶ አበበ ዘውዱ – ስ/ቁ. 0913717096 ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply