የጀግኖቹ እሸቴ ሞገስ እና የልጁ ይታገሱ እሸቴ የጀግንነት እና የቤተሰብ ታሪክ ላይ ያተኮረው መጽሐፍ ተመረቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ…

የጀግኖቹ እሸቴ ሞገስ እና የልጁ ይታገሱ እሸቴ የጀግንነት እና የቤተሰብ ታሪክ ላይ ያተኮረው መጽሐፍ ተመረቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጀግንነት የተሰውት የጀግናው እሸቴ ሞገስና የልጁ ይታገሱ እሸቴ የጀግንነት እና የቤተሰብ ታሪክ የያዘ ❝ሞትን ያስበረገጉ ጀግኖች❞ መጽሐፍ ዛሬ በአዲስ አበባ ተመርቋል፡፡ በደራሲ ካፒቴን አልዓዛር አያሌው የተጻፈው ይህ መጽሐፍ 520 ገጾችን የያዘ ሲሆን ሞትን ያስበረገጉ ጀግኖች በወቅቱ አሸባሪው ሕወሓት ወደ አዲስ አበባ በመገስገስ ላይ በነበረበት ወቅት ጀግኖቹ እሸቴ ሞገስ እና ልጁ ይታገሱ እሸቴ የፈጸሙትን አስደናቂ ጀብድ ያስረዳል። ደራሲው ካፒቴን አልዓዛር አያሌው የእነ እሸቴ ሞገስን ታሪክ ልዩ የሚያደርገው በታሪክ እና በማስረጃ መሰነዱ መኾኑን ጠቅሰዋል። በተደረገው ተጋድሎ ጀብድ የፈጸሙ በርካታ ጀግኖች መኖራቸውንም ተናግረዋል። ጀግኖቹ እሸቴ ሞገስ ልጃቸው ይታገሱ እሸቴ ጋር በመኾን በሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዘጠኝ አባላትን በጀግንነት በመረፍረፍ በክብር መሰዋታቸው ይታወሳል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply