የጀግኖቹ እሸቴ ሞገስ እና ይታገስ እሸቴ የአስከሬን ሽኝት ጥር 1 ቀን 2014 ይካሄዳል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጀግኖቹ እሸ…

የጀግኖቹ እሸቴ ሞገስ እና ይታገስ እሸቴ የአስከሬን ሽኝት ጥር 1 ቀን 2014 ይካሄዳል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጀግኖቹ እሸቴ ሞገስ እና ይታገስ እሸቴ የአስከሬን ሽኝት ጥር 1 ቀን 2014 የሚከናወን መሆኑን ቤተሰብ አስታውቋል። የአቶ እሸቴ ወንድም ዶ/ር ይተብቱ ሞገስ አሚማ ወደ የካ አባዶ መኖሪያ ቤታቸው ባቀናበት ወቅት እንደገለጹት የጀግኖች የአስከሬን ሽኝት ከሳላይሽ ወደ ሸዋሮቢት መኖሪያ ቤታቸውና ከዛም ወደ ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ዘመድ፣ አድናቂዎችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት ለማከናወን እቅድ ተይዟል። በቤተሰብ በኩል የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዳለ ሆኖ መንግስትና ሌሎች አደረጃጀቶችም ማገዝ በሚችሉት መንገድ ሁሉ እንዲደግፉ ጥሪ ቀርቧል። ጀግኖቹ አባትና ልጅ እሸቴ ሞገስ እና ይታገስ እሸቴ ሳላይሽ ላይ 9 አሸባሪዎችንና ወራሪዎችን ገድለው ከመሰዋታቸው ባሻገር አቶ እሸቴ ሞገስ የሰሩትን ጀብድ መዝግብ እያሉ ለትውልድ ማስቀረታቸው የብዙዎችን ቀልብ ስቧል፤ አስመስግኗቸዋል፤ ከፍ ብሎም እየተነገረላቸው ነው። አቶ እሸቴ ሞገስ በ56 ዓመት፣ ልጃቸው ይታገስ እሸቴ ደግሞ በ31 ዓመታቸው ነው በደም እና በአጥንታቸው ለትውልድ የሚበጅ የማይሞት ታሪክ ሰርተው የተሰውት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply