You are currently viewing የጁንታውን አዋጊ ጨምሮ ከ20 በላይ የጁንታው ታጣቂዎችን ከገደሉ በኋላ  ከሌሎች ጀግኖች ጓዶቻቸው ጋር በክብር የተሰውት በሸዋ የመኮይ ጀግና_አቶ አበበ በነበረ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የጁንታውን አዋጊ ጨምሮ ከ20 በላይ የጁንታው ታጣቂዎችን ከገደሉ በኋላ ከሌሎች ጀግኖች ጓዶቻቸው ጋር በክብር የተሰውት በሸዋ የመኮይ ጀግና_አቶ አበበ በነበረ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የጁንታውን አዋጊ ጨምሮ ከ20 በላይ የጁንታው ታጣቂዎችን ከገደሉ በኋላ ከሌሎች ጀግኖች ጓዶቻቸው ጋር በክብር የተሰውት በሸዋ የመኮይ ጀግና_አቶ አበበ በነበረ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሌላኛው ስለሀገርና ስለወገን ሲል ውድ ህይወቱን አሳልፎ የሰጠ የሸዋ አርበኛ አቶ አበበ በነበረ ይባላሉ፤ የ58 እድሜ ባለፀጋ ናቸው። በአንፆኪያ ገምዛ የመኮይ ከተማ ነዋሪ ናቸው። በአንጾኪያ ገምዛ መኮይ ወረዳ ላይ የህወሓት ወራሪ ሀይል እንዳይገባ ምሽግ ሰርተው ለአንድ ወር ያክል ከጓደኞቻቸው ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል አድርገዋል። ባደረጉት ተጋድሎም መኮይን ጠላት በአይኑ ሳያያት በእግሩ ሳይረግጣት እና ሳያወድማት ማዳን ችለዋል። ህዳር 23 ቀን 2014 ሀሙስ ቀን ከጁንታው ጋር ባደረጉት ተጋድሎ አቶ አበበ በነበረ የጁንታውን አዋጊ ጨምሮ ከ20 በላይ የጁንታው ታጣቂዎችን ከገደሉ በኋላ ከሌሎች ጀግኖች ጓዶቻቸው ጋር በክብር ተሰውተዋል። እያንዳንዱ የትውልድ ጀግኖች በሚከፍሉት መሰዋዕትነት ኢትዮጵያ በክብር ትኖራለች !! ክብር ለህልውናችን ሲሉ መስዋዕትነት ለከፈሉት አርበኞቻችን !! ምንጭ_የሰሜን ሽዋ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የዲጂታልና የማህበራዊ ሚዲያ ክፍል!

Source: Link to the Post

Leave a Reply