You are currently viewing “የጁንታው ሀገር አፍራሽ ኃይል ለመከላከል እና ለመመከት ወጣቱ ብቁ ብቃት እንዳለው አልጠራጠርም” አቶ መኳንንት ደሳለኝ_የደባርቅ ከተማ ነዋሪ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…    ነሀሴ 10…

“የጁንታው ሀገር አፍራሽ ኃይል ለመከላከል እና ለመመከት ወጣቱ ብቁ ብቃት እንዳለው አልጠራጠርም” አቶ መኳንንት ደሳለኝ_የደባርቅ ከተማ ነዋሪ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሀሴ 10…

“የጁንታው ሀገር አፍራሽ ኃይል ለመከላከል እና ለመመከት ወጣቱ ብቁ ብቃት እንዳለው አልጠራጠርም” አቶ መኳንንት ደሳለኝ_የደባርቅ ከተማ ነዋሪ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሀሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የደባርቅ እና አካባቢው ወጣቶች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ከአማራ ልዩ ኃይል እና ከሚሊሻ አባላት ጎን በመሆን የተለያዩ በሮችን በመዝጋት ጁንታውን ለመቅበር ዝግጁ መሆናቸውን ያነጋገርናቸው ወጣቶች ገልፀዋል፡፡ ወጣት ሙሉስሜን ሞላ እና ወጣት አዲሱ የደባርቅ ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ የጠላታችን ጁንታው አባላት ወረራ ከጀመረ ሰነባብቷል፤ሆኖም ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባስቦ ደባርቅ ከተማ ለመግባት የሚያደርገውን ጥረት ለማክሸፍና ከዛው ካለበት ውጦ ለማስቀረት መነሳታቸውን ተናግረዋል፡፡ ወጣቱ ከእጁ ባለው ጦር ፣ጎራዴ ፣ካራና ሌሎች መሳሪያዎችን በመያዝ በደባርቅ ዙሪያ ባሉ መግቢያ በሮች ተደራጅቶ እየጠበቀ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ሌላው የደባርቅ ከተማ ነዋሪ ወጣት ገብሬ ጌትነት 2 F1 ቦንቦችን በመያዝ የተለከፈ ውሻ የሚመስለውን የጁንታ ጠላትን ድባቅ ለመምታት እና ከገደሉ ውስጥ ለመቅበር መዘጋጀቱን ተናግሯል፡፡ የደባርቅ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰለሞን ተዘራ በከተማው ከ4 ሺ በላይ ወጣቶች ወታደራዊ ስልጠና የወሰደ ሲሆን ደባርቅ እና አካባቢውን ለመጠበቅ ተነሳሽነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህን ብቻ ሳይሆን የአማራ ድንበሩ ተከዜ ጫፍ በመሆኑ የስሜኑን ቀጠና ለመጠበቅ ሙሉ ኃላፊነቱን ወስዶ ሌት ከቀን እየጠበቀ ይገኛል ብለዋል፡፡ ወጣቱ አካባቢውን ከመጠበቅ ባለፈ በከተማው ፀጉረ ልውጥን በመፈተሸ እና በበጎ አድራጎት በመሳተፍ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ የደባርቅ ከተማ ነዋሪና ባለሃብት የሆኑት አቶ መኳንንት ደሳለኝ ጀራምባ በተባለ መግቢያ በር ተገኝተው ወጣቱን ሲያበረታቱ ተመልከተናል፡፡ የጁንታው ሀገር አፍራሽ ኃይል ለመከላከል እና ለመመከት ወጣቱ ብቁ ብቃት እንዳለው አልጠራጠርም ሲሉ አቶ መኳንንት ገልፀዋል፡፡ የከተማችን ወጣቶች በሁለንተናዊ ተሳትፎ በማድረግ እየሰጠ በመሆኑ ለምስጋና ቃላት ያጥረኛል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ወጣቶቹ ለጠላት አይበገሬነታቸውን እና ቁርጠኝነታቸውን በፉከራና በሽለላ ስሜታቸውን ገልፀዋል፡፡ ጀግኒት ሴት ወጣቶችም የዘመቻው አካል ሆነው ተመልክተናል፡፡ ዘገባው የደባርቅ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply