የጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲቲዩት ለሁለንተናዊ የሃገር እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡የኢንስቲቲዩቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቱሉ በሻ እንደገለፁት ለሃገር ደህንነት…

የጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲቲዩት ለሁለንተናዊ የሃገር እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

የኢንስቲቲዩቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቱሉ በሻ እንደገለፁት ለሃገር ደህንነት እና ልማት ወሳኝ በሆኑ መስኮች ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልፀዋል::

ዳይሬክተሩ አክለውም ዘርፉ ለአገር እድገት እና ብልፅግና ወሳኝ ሚናን የሚጫወት በመሆኑ በቀጣይ 10 አመታት የሚተገበሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ነድፎ ለተፈፃሚነቱ እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል::

የኢኒስቲቲዩቱ የኢኖቬሽን እና አናሊቲክስ ማእከል ሃላፊ አቶ ሙሉአለም የሺጥላ ጊዜውን ያማከለ እና ሃገራችንን ከአፍሪካ ቀዳሚ ያደረጋትን የምርምር ቁሳቁስ እየተጠቀመ ያለው ኢንስቲቲዩቱ በትምህርት ጤና ግብርና የከተማ እና ገጠር ልማት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ገልፀዋል::

ኢትዮጲያ ይህን ተቋም በመመስረት ከአፍሪካ ቀዳሚ እንደነበረች ያስታወሱት ሃላፊው ተቋማቸው በቀጣይ አመታት ወደስራ የሚያስገባው እቅድ ተጨባጭ ለውጦች እንዲመጡ የሚያደርግ መሆኑንም ገልፀዋል::

አብዱልሰላም አንሳር
ታህሳስ 15 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply