You are currently viewing የጅማ ሀገረ ስብከት ተሽከርካሪዎቹን እንዳያንቀሳቅስ ታገደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 22 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከ…

የጅማ ሀገረ ስብከት ተሽከርካሪዎቹን እንዳያንቀሳቅስ ታገደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከ…

የጅማ ሀገረ ስብከት ተሽከርካሪዎቹን እንዳያንቀሳቅስ ታገደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከተወሰዱበት ተመልሰዋል። ዛሬ ማለዳ 12:30 ላይ መኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ ኀይል ተከብቦ የተወሰዱት የጅማ ፣ የየም እና የኮንታ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልከአ ሰላም ተስፋ ሚካኤል አሰፋ፣ ከተወሰዱበት ተመልሰዋል። የጸጥታ ኀይሉ ዋና ሥራ አስኪያጁን ከወሰዳቸው በኋላ፣ የሀገረ ስብከቱ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ መኾኑን፣ ከበላይ አካል የተሰጠ ነው ያለውን ትእዛዝ በመጥቀስ አስታውቋቸዋል፤ ተብሏል። የዋና ሥራ አስኪያጁም መኖሪያ ቤት በጸጥታ አካሉ ቪዲዮ እየተቀረጸ ፍተሻ እንደተካሔደበት ተገልጿል። ዋና ሥራ አስኪያጁ ዛሬ ማለዳ መኖሪያ ቤታቸው ተፈትሾ ከመወሰዳቸው አስቀድሞ፣ በዛሬው ዕለት በሚከበረው የቅዱስ ዑራኤል በዓል ላይ ለመገኘት፣ ወደ ደብረ በረከት ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ለማምራት እየተዘጋጁ የነበረ ሲኾን፣ በአሁኑ ወቅት ከተወሰዱበት ተመልሰው በደብሩ እንደሚገኙ ታውቋል ሲል የዘገበው የማህበረ ቅዱሳን ብሮድ ካስት አገልግሎት ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply