የጅማ አባጅፋር ቤተመንግስት በቅርስ ጥገና ባለሙያ ዕጥረት ምክንያት መጠገን እንዳልተቻለ ተገለጸ።

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ከበደ ዲሳሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የቅርስ ጥገና ባለሙያ በሚያስፈልገው ልክ አለመኖሩ ጉዳት የደረሰባቸውን ቅርሶች ማስጠገን አልቻልንም።

በተለይም ደግሞ በዕድሜ መጨመር ምክንያት ጉዳት ላይ ያለውን የጅማ አባጅፋር ቤተመንግስትን በተደጋጋሚ እድሳት እንደሚደረግለት ብንናገርም የቅርስ ባለሙያ ባለመኖሩ ልናስጠግን አልቻልንም ብለዋል፡፡

ረጅም አመታትን ያስቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናት መስጅዶችን ጨምሮ የንጉስ ኩምሳ ሞሮዳ ቤተመንግስት በዕድሜ መጨመር ምክንያት ለጉዳት ተዳርገዋል ሲሉ አቶ ከበደ ነግረውናል፡፡

በቢሮው አቅም ሊሰሩ የሚችሉ እንደ መልካ ቁንጡሬ መካነ ቅርስ ያሉትን በአቅማችን ጥበቃ አድርገናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በመቅደላዊት ደረጀ
ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply