
የጅማ ደብረ ኤፍራታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በሌሉበት አይመረቅም! የጅማ ኦርቶዶክሳውያን በዛሬው ዕለት ለዓመታት የለፉባትንና ቅዳሴ ቤቷ ይከበራል ተብሎ በተጠበቀው የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ሲጠብቁ ቢውሉም ከአባታቸው ጋር ሳይገናኙ ቀርተዋል። የጅማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በስፍራው ስለማይገኙ ቆሞሳት ባርከው ቤተ ክርስቲያኗ ትመረቅ ቢባሉም ምዕመናኑና ማኅበረ ካህናቱ እሳቸው የደከሙበትን ቤተ ክርስቲያን በሌሉበት አናስመርቅም፤ ይህ የኛ ቀን ነው፤ በእግዚአብሔር ቀን አባታችን ባሉበት እናስመርቃለን፤ የሠራነው የእግዚአብሔርን ቤት ነው ለምን ተፈተንን አንልም ብለዋል። የቤተ ክርስቲያኑ ምርቃት ወደ ሌላ ቀን መዘዋወሩንም የደብሩ አስተዳዳሪና አሠሪ ኮሚቴው ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይፋ አድርገዋል። ነገ በዓለ ንግሷ በቀድሞ ቤተ ክርስቲያን (በመቃኞ) ተከብሮ ይውላል። በተያያዘ ብፁዕነታቸው በዚህ ሰዓት አዲስ አበባ ገብተዋል። © ማኅበረ ቅዱሳን
Source: Link to the Post