የጆ ባይደን አሸናፊነት በመራጭ ወኪሎች ተረጋገጠ

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሸናፊነታቸው በአገሪቱ መራጭ ወኪሎች ስብስብ ተረጋገጠላቸው፡፡ኤሌክቶራል ኮሌጁ የባይደንን ድል ማረጋገጡን ተከትሎ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ባደረጉት ንግግር “የዩናትድ ስቴትስ ዴሞክራሲ ተገፍቶ፣ ተፈትኖ እና ስጋት ላይ ወድቆ ነበር” ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ዴሞራሲያችን “የማይበገር፣ እውነተኛ እና ጠንካራ” መሆኑን አሳይተናል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡የምርጫውን ውጤት ለማስቀየር ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሄዱትን ርቀት ያወገዙት ባይደን፤ በመጨረሻም የሕዝቡ ፍላጎት ማሸነፉን ነው የተናገሩት።

በኅዳሩ ምርጫ ባይደን 306 የግዛት ወኪሎችን ድምጽ ያገኙ ሲሆን ትራምፕ ደግሞ 232 ማግኘታቸው አይዘነጋም፡፡የኤሌክቶራል ኮሌጁ ማረጋገጫ ባይደንን ወደ ነጩ ቤተመንግሥት ለማስገባት ከሚያስፈልጉ ወሳኝ እርምጃዎች አንዱ መሆኑን የጠቆመው የቢቢሲ ዘገባ፤ አወዛጋቢው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግን አሁንም የምርጫውን ውጤት አልቀበልም በሚል አቋማቸው እንደጸኑ አስታውሷል፡፡የኤሌክቶራል ኮሌጁ ውጤት ከተሰማ በኋላም “በምርጫው የተፈጸመ ማጭበርበር ስለመኖሩ የሚያሳይ ማስረጃ የለም” ያሉትን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዊልያም ባርን እንዳሰናበቷቸው በትዊተራቸው አሳውቀዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply