የገበያ አሻጥርን እየተከላከልኩ ነዉ፤የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር!የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኮኖሚ አሻጥርና ኑሮ ውድነት መከላከል ግብረ ኃይል የዘመን መለወጫ የገበያ አቅርቦትን ገ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/MZFPx8B4myF8k5l3eI_v78K1j_LpFdslzTK8hYP1WyyyO98CjTzwrLQV1ozijbz433sKxPqSV6SrGbUrWEHQ4M683yVmp0kzSQKAgr8atg1hp_PnXsRUZOm2H1D2d7LuUF4wBsGP3nhDzphHHYJ-sNxuYryK_2OokEVYlkFXSItcyMdOZSoYMSCFxpHHlEWLIyI7Qhsvn3SDYGsWhFUh11tYOEI39dORc-lzQeU3S_wgRR-0QRd4qIsxHrUyhRYxc8ev7TalNPnYP9-DBbjJATn5zSNEanvB7J5ZspXrhdCc3aX29dqa8ZgtH8PkwJ2ExNSegA6I1wcvp_FiNYZdIg.jpg

የገበያ አሻጥርን እየተከላከልኩ ነዉ፤የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኮኖሚ አሻጥርና ኑሮ ውድነት መከላከል ግብረ ኃይል የዘመን መለወጫ የገበያ አቅርቦትን ገምግሟል።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እንዳሉት፣ በዘመን መለወጫ የገበያ አቅርቦት እና የገበያ ዋጋ የታዩ ችግሮችን ለመፍታት ከክልል አምራቾች፣ ከማህበራትና ከባዛር ጋር በማስተሳሰር በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ተደርጓል፡፡

በስኳር እና በስሚንቶ ላይ የገበያ አሻጥር የፈፀሙ ግለሰቦች ላይም ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

ለመጪዎቹ የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላትም ከባለፈው በዓል ተሞክሮ በመውሰድ በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከሥራ፣ ኢንተርፕራዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተገኘዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ፣የዘመን መለወጫ በዓል ላይ የምርት አቅርቦት ላይ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም፣ በመጪው በዓላት የምርት ዋጋን ለመቀነስ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አቶ ጃንጥራር አሳበዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያያን
መስከረም 07 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply