የገባናቸውን ቃልኪዳኖች ታማኞች ከሆንን የኢትዮጵያን ድል እናበስራለን-ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013  የገባናቸውን ቃልኪዳኖች ታማኞች ከሆንን የኢትዮጵያን ድል እናበስራለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ ገለፁ ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸውም የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ በሚል ማኅበረሰብ ውስጥ ነው ያደግነው ቃል ኪዳን የዓለም ህልውና የተመሠረተበት ሥርዓት ነው ሰው ከሰው ሰው ከአካባቢው አካባቢ እርስ በርሱ ተጠባብቆና ተግባብቶ የሚኖረው በቃል ኪዳን ነው ብለዋል፡፡

ድል የገቡትን ቃል በማክበር፣ ለቃል ታምኖ በመሥራትና ቃልን በተግባር በመግለጥ የሚገኝ ነው። ለኢትዮጵያም የገባነውን ቃል ኪዳን አድሰንና አክብረን፣ የኢትዮጵያን ድል እናበሥራለን” ብለዋል። መንግሥትና ሕዝብ የሚኖሩት በቃል ኪዳን ነው፤ እንደ መንግሥትና እንደ ሕዝብ ለገባናቸው ቃል
ኪዳኖች ታማኞች ከሆንን ሀገር ሰላም፣ ምቹና ባለጸጋ ትሆናለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ። የድል ቃል ኪዳን ብስራት ቀን በአዲስ አበባ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ወጣቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በመሐል ማዘጋጃ ቤት አዲስ አበባ ተከብሯል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply