የገና በዓልን ለማክበር የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ስላልቀረቡልኝ በዓሉን ለማክበር ተቸግሬያለው ሲል የሙዳይ በጎ አድራጐት ማህበር አስታወቀ፡፡

የገና በዓልን ለማክበር የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ስላልቀረቡልኝ በዓሉን ለማክበር ተቸግሬያለው ሲል የሙዳይ በጎ አድራጐት ማህበር አስታወቀ፡፡

ከ1 ሺ በላይ የሚሆኑ እናቶች፣ ወጣቶች፣ ህጻናትና አረጋዊያን በማህበሩ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

የማህበሩ መስራች ወይዘሮ ሙዳይ ምትኩ ለአሀዱ እንደተናገሩት የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ የሚደረገው ድጋፍና እርዳታ በመቀነሱ የእለት ጉርስም ለማግኘት መቸገራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ማህበሩ ከተመሰረተ ከ20 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን በየዓመቱ በዓል ሲመጣ ማህበረሰቡ የአቅሙን ያህል የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ ያደርግ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

በዓልን ለማክበር የሚያስችሉ አስፈለጊ የምግብ ግብዓቶች ቀደም ብለው በዚህ ሰዓት  ወደማህበሩ ይገባ እንደነበር ያስታወሱት ወይዘሮ ሙዳይ አሁን ላይ የገና በዓልን ለማክበር የሚያስችል ምንም አይነት ድጋፍ እየተደረገ ባለመሆኑ መቸገራቸውን ገልጸዋል፡፡

የማህበሩ መስራች ወይዘሮ ሙዳይ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፎችን ማድረግ የአንድ ሰሞን ተግባር ሊሆን እንደማይገባ ጠቁመው ግለሰቦችም ይሁን ድርጅቶች የገና በዓልን ለማክበር የሚያስችል እርዳታና ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

**************************************************************************

ቀን 27/04/2013

ምስል፡- የማህበሩ ሎጎ

Source: Link to the Post

Leave a Reply