የገና በዓል ከጦር ጉዳተኞች ጋር እየተከበረ ነው

የገና በዓል ከጦር ጉዳተኞች ጋር እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የገናን በዓልን ከጦር ጉዳተኞች ጋር እያከበረ ነው።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአካል ጉዳተኞችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ተሳታፊነትን ማረጋገጥ ኃላፊነቱ መሆኑን ገልጿኣል።

በመሆኑ ይህንን ዓለማ ተግባራዊ ያደረገ የበዓል ፕሮግራም ከጦር ጉዳተኞች ጋር እያከበረ ይገኛል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የቀደሞ እና የአሁን የጦር ጄኔራሎች እና ከ141 በላይ የጦር ጉዳተኞች በዓሉን እያከበሩ ይገኛሉ፡፡

በበአል ፕሮግራሙ ላይ ቀደም ሲል የነበሩትና ፈርሰው የነበሩ የብሄራዊ ጀግኖች አምባ እና የህጻናት አምባ ማህበራት መልሶ መቋቋሙም ተነግሯል፡፡

ሌላው የፕሮግራሙ ዓላማ የቀደሙት እና አሁን ያሉት የጦር ጉዳተኞች ተጠቃሚ የሚያደርጉ እቅዶችም ተነድፈዋል፡፡

በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የፌዴራል ፖሊስ ከሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለዚህ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በፈቲያ አብደላ አና ፍሬ-ህይዎት ሰፊው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የገና በዓል ከጦር ጉዳተኞች ጋር እየተከበረ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply