የገንዳውሃ ከተማ ተማሪዎች የ’በቃ’ #NoMore ዘመቻ ሰልፍ አካሄዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሜሪካ እና ምዕራባውያን ሀገራ…

የገንዳውሃ ከተማ ተማሪዎች የ’በቃ’ #NoMore ዘመቻ ሰልፍ አካሄዱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሜሪካ እና ምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫናና ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በገንዳውሃ ከተማ አስተዳደር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተካሂዷል። ሠልፈኞቹ አሜሪካ እና ምዕራባዊያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት ሰልፈኞቹ አውግዘዋል። በስልፉ ፕሮግራም በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በንግግራቸው ነፃነትን ማንም አይሰጠንም፤ ነፃነት የሚገኘው ደም በመገበር በመሆኑ ለሁለንተናዊ ትግል መነሳት አለብንብለዋል። የአማራ ህዝብ ከፍታ ዝቅ እንዲል ሲሰሩ የነበሩ የህውሃት አመራሮች ዛሬም አማራን ለማጥፋት ቆርጠው በመነሳት እና የሀገር መከላከያን በማጥቃት የጀመሩ መሆናቸው ተወስቷል፤ ይህን እኩይ ስራ ለመቀልበስም የአማራ ልጆች መከላከያን መቀላቀል ይኖርባቸዋል ተብሏል። አስተዳዳሪው አክለውም የትግራይ ወራሪ ሃይል አማራ ጠል በመሆኑ በወረራቸው አካባቢዎች ያደረሰውን በደል ግምት ውስጥ በማስገባት ህዝባችን ላይ ለወደፊት ሊከሰት የሚችለውን ችግር ከወዲሁ በማሰብ መዘጋጀት ይኖርብናል ብለዋል። ድል የሚገነው በምኞት አይደለም፤ ድል የሚገኘው ምቾትን እየመረጡ አይደለም፤ ድል የሚገኘው የጥይት ድምፅ ሳንሰማ አይደለም። በመሆኑም ተደራጅተን እና ትግል አድርገን ድሉን እናስመዘግባለን፤ አማራንም ከወራሪው ነፃ እናወጣለን ብለዋል። በጎንደር ዩንቨርሲቲ ረ/ፕሮፌሰር ገብሬ ሙሉዓለም በንግግራቸው የትግራይ ወራሪ ሃይል ስሪቱ አማራ ጠል እና አልጠግብ ባይ በመሆኑ በደረሰበት ሁሉ የግፍ ግፍ ፈጽሟል ብለዋል። ይህ ደግሞ የማንረሳው በደል በመሆኑ ህዝባችን ነፃ ለማውጣት መክፈል ያለብንን መስዋዕት በመክፈል ድል እናደርጋለን ሲሉ አክለዋል። ምንጭ_ምዕራብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲን ጠቅሶ ገንዳውሃ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply