የገዛ ቀጣሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።ወንጀሉ የተፈጸመው ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 10:45 ሰዓት ሲሆን ቦታው…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/GO73SBBhOCIbnRTcdYPlL7x-KEjnr04TBseNR-yPzXQdG4Yk_5e6wMzgzmqsdJZfBWFt659B4564EuovyBfBinteR7VOwo5SbOkHvRPCsznNHV2xLKTLkZPx9Yok95HpsLzDPVAWA4wHEyG28NFN8I5DR_-I3Q0fskxkBJ9-HmOGZA8XuXyFJCwHDSNfhqcBKzPLO5C4K-abgMHBH9QCxH1vB0GSUJWBEJs3IutBgSyk9H52lYkyI9b5hWnTE6CAxxqUR9D5fKt0NRD8qBTSyRAm4t83SAuHgoZgF0uuV_FVSUJXBgEzz9IxeTgVFhVjwaFe7yPRXyyFxkunCO542A.jpg

የገዛ ቀጣሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ወንጀሉ የተፈጸመው ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 10:45 ሰዓት ሲሆን ቦታው ደግሞ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው አስኮ ሊዝ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።

ተከሳሽ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ከምትሠራበት ከወ/ሮ ፋሲካ ተሾመ ቤት ሲሆን በመሃላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ሟችን በቡና ዘነዘናና በስለት የተለያዩ የሰውነት አካላቸው ላይ ጉዳት በማድረስ የመግደል ወንጀል ፈጽማለች።

ፖሊስ መረጃው ከህብረተሰቡ ከደረሰው በኋላ በአደረገው ብርቱ ፖሊሳዊ ክትትልና ምርመራ ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ከፈጸመች ከሦስት ቀናት በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሏን ገልጾ ምንም እንኳ የፖሊስ ተግባር ወንጀልን አስቀድሞ መከላከል ቢሆንም ተፈጽሞ ሲገኝም ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ተጠርጣሪዎችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚቻል ገልጿል።

ህብረተሰቡ የቤት ሠራተኞችን ሲቀጥር በቂ ዋስትናም ማቅረብ እንዳለባቸው ጭምር ሊያስገድድ እንደሚገባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
የኢትዮጵያውያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply