You are currently viewing “የ”ጉልበቴን ልፈትሸው” እና ጠላት ፍለጋ ፖለቲካ ውድቀት እንጂ ውጤት አላመጣልንም፣ አያመጣልንም!” ሲል እናት ፓርቲ ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም…..

“የ”ጉልበቴን ልፈትሸው” እና ጠላት ፍለጋ ፖለቲካ ውድቀት እንጂ ውጤት አላመጣልንም፣ አያመጣልንም!” ሲል እናት ፓርቲ ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም…..

“የ”ጉልበቴን ልፈትሸው” እና ጠላት ፍለጋ ፖለቲካ ውድቀት እንጂ ውጤት አላመጣልንም፣ አያመጣልንም!” ሲል እናት ፓርቲ ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ በያዝነው 21ኛው ክፍለ ዘመን እንኳንስ አንድ ሀገር ውስጥ ያሉ በሀዘን በደስታ የሚገናኙ ወንድማማቾች ቀርቶ በጠላትነት ይተያዩ የነበሩ ሀገራት ብዙ ሺህ ማይሎችን እያቋረጡ የአንዱን ጎደሎ ሌላው ሞልቶ የሕዝባቸውን አኗኗር ብሎም ዓለሙን ለመቀየር የሚታትሩበት/የሚጣጣሩበት ጊዜ ነው ብሏል እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጠው መግለጫ። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሌላውን እንኳን አቆይተነው በቅርቡ የመጣውን “ለውጥ” እንኳን ብንወስድ “ፍጹም አይቻልም” የተባለውን ያስቻለው በአንድ ግንባርና ምሽግ ባይገናኙም ነቀምቴ በወደቀው ለውጥ ናፋቂ ጎንደር ያለው “ደሜ ነው” ብሎ እዚያና እዚህ በተለያየ ጉድጓድ ግን ለአንድ ዓላማ ስለወደቁ ወዲህም መሪዎቹ “የወጣቶቻችን ደም በከንቱ ፈሶ እንዳይቀር አንተ ትብስ…” በመባባላቸው ነው ሲል ገልጧል። የእነዚህ ማኅበረሰብ በጎ ትሥሥር ኹሉ “እሳትና ጭድ” ሳይሆን ለኢትዮጵያ መዳን አርማ ነው ብሎታል። እናት ፓርቲ ሲቀጥል ግንኙነቱ በቀና ጎዳና ያልሄደባቸው ጊዜያት ቢመረመሩ ለሴራ ፖለቲካ ትርፍና የአስተዳደራዊ አቅመ ቢስነቶች መሸፈኛነት የዋሉ ኾነው እናገኛቸዋለን ብሏል። የሞትና ስደት ዜናው እየዋጣት ነው ያለው እናት ፓርቲ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ፣ አሞራ ቤት ቀበሌ፣ ልዩ ቦታው አውራ ጎዳና በተባለ አካባቢ በጸብ ያለሽ በዳቦ የተነሳው ጉልበት ፍተሻም የዚኹ አካል እንጂ ብዙ እንደብርቅ የሚታይ ሰበር ዜና አይደለም ሲል አክሏል። የዚኽ ክስተት አንድ ልዩ ነገር ቢኖረው አዝሎት የመጣው አደጋ ጥልቀት ያለውና በአፋጣኝ ሃይ ካልተባለ ሀገራችንን ሌላ የግጭት አዙሪት ውስጥ የማስገባት አቅም ያዘለ ስለመኾኑም ጠቅሷል። ፓርቲው ባደረገው ሰፋ ያለ ማጣራት ከፌዴራል መንግስት በቂ ትኩረት የተነፈገው ነገር ግን በኹለቱ ወንድማማች ማኅበረሰቦች መሐል አኹንም በአቅመ ቢስ ፖለቲከኞች ከፍተኛ ቤንዚን አርከፍካፊነት ለከፋ እልቂት የሚዳርግ ኾኖ አግኝተነዋል ነው ያለው። ቃላት ሳይመረጥ ይወረወራል፣ ይዛታል፣ በአቅራቢያ አካባቢዎች ከፍተኛ የሚባል የታጠቀ ኃይል ጭምር እየሠፈረ ይገኛል ሲል እናት ፓርቲ ገልጧል። በአጠቃላይ ፖለቲካችን ጥቂት የቡድን መሣሪያ ሲታጠቁ “ጉልበት ፍተሻ” የሚገባበት፣ ስክነት አልባ፣ የግድ ጠበኛ ፈላጊ ቢኾንም እንዲህ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከቢሯቸው ግድግዳ ሻገር ብለው በማያዩ ገዥዎች የደም አበላ ውስጥ መዘፈቋ ግን ይበቃል፣ ይበቃናል ብሏል። ሺዎችን ጭዳ አድርጎ ስልጣን ላይ መረማመድ ያረጀ ያፈጀ ስልት እንደኾነ፣ የሰሜኑን ጠላት ቆም አድርጎ በሌላ ግንባር ሌላ ጠላት የመፈለግን “አዝማሚያ” ቢያንስ ከሕዝባችን የማይሰወር ምሥጢር እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል ያለው ፓርቲው ምን አልባት ሚዲያው፣ ሀብቱ፣ መሣሪያው፣… “ኹሉ በእጄ…” ተብሎ ይታሰብ ይኾናል። ትሕነግም እንዲሁ ነበረው፤ ምኒልክ ቤተ መንግስትን ግን የተሰናበተው በተጣመረ እጅና በመሪር እንባ ብቻ ነው ሲል አስጠንቅቋል። ፓርቲው የሚከተሉትን ምክረ ሀሳቦችንም ጠቁሟል፡- ፩. ፌዴራል መንግስት ሊመጣ ያለውን ችግር “በልኩ” ተረድቶ “ማዕከላዊነቱንና ሚዛናዊነቱን” ጠብቆ አፋጣኝና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ፣ የዜጎችን በሰላም የማስከበር ቀዳሚ መንግሥታዊ ግዴታውን እንዲወጣ እንጠይቃለን። ፪. የተቋምና የአስተሳሰብ ግንባታ ጊዜ ወሳጅነቱን ብንረዳም ቅሉ “አንድ ወጥ ነኝ” እያለ ሊያሳምነን የሚደክመው ብልጽግና(ፓርቲ) ከጠቅላላ ጉባኤ show off ዘለል ያለ የቤት ሥራ እንደሚቀረው ለማወቅ ውስጥ አዋቂም ነቢይነትም አይሻም። ታዲያ የመጋረጃ ጀርባ ቁርቁሶቹን ወደ መላው ሕዝብ መድፋት አደጋው ለሀገር፣ ለራሱ ለድርጅቱና ባለስልጣናቱ፣ ጠበብ ሲልም ለልጆቻችሁ ነውና በጥልቀት ዐይታችሁ ፍቱት፤ ይኼ ጊዜ ይጠይቃል ከተባለም ቢያንስ ገመናችሁን ሸፍኑ ለማለት እንወዳለን። ፫. የሕዝብ አገልጋይ ተብላችሁ በዙፋኑ የተቀመጣችሁ በተለይ የክልል ርእሳነ መስተዳድር እናንተ በምትወረውሩት የቃላት ቀስት የመትነድፉትና የምትጥሉት እየበዛ ነውና ራሳችሁን ግዙ፣ ወይም “በቃኝ አልቻልኩም” ማለትን ልመዱ፡፡ ሕዝብ ኹሉንም ሰቆቃ ስለታገሰ እንዴት ለዳግም ጦርነት ታዘጋጁታላችሁ? ፬. የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች እንዲህ ባሉ ወቅቶች “ተው” የሚል ድምጻችሁ ያስፈልገናል። ትሕነግም ሙሉ ለሙሉ ጦርነት ውስጥ ከመግባቱ በፊት በየቦታው ከመተንኮስ፣ ቃላት እየመረጠ ፌዴራል፣ የክልል መስተዳድሮችንና ሕዝብን ሲያበሻቅጥ የነበረው። ፭. እናት ፓርቲ የፌዴራል አወቃቀሩ የብዙ ችግሮቻችን ምንጭ ነው ብሎ ያምናል። አማራጭና የተሻለ የፌዴራል አወቃቀር ይገባናል፣ ደግሞም አለን። እንዲህ ያሉት ጉዳዮች ጥልቅ ውይይት ይፈልጋሉ ቢባል እንኳን “የክልል ልዩ ኃይሎች” አወቃቀርን በጥናት ገምግሞ አስፈላጊውን ማስተካከያ ማድረግ ካልተቻለ በአኹኑ አካሄድ ደግማዊ “ጥቅምት ፳፬” ሩቅ እንዳልኾነ አመላካቾች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ሕዝብ ጠላት እየተፈለገ፣ ግንባር እየተቀያየረ የጦርነት አዙሪት ውስጥ መኖር ይበቃዋል፡፡ ቢያንስ ብልጽግና ከኢሕአዴግ እንደሚለይ በኹለት ነገሮች ያስመስክር:_ “አንድን ቡድን” መርጦ ከማጀገን መውጣት እና በረከታዊ “ያለጠላት አልኖርም” ባይነትን አንቅሮ መትፋት፡፡ ፓርቲያችን እናት በንግግር የማይፈታ ችግር የለም የሚል ጽኑ እምነት አለው። “ራሳችኹን ግቱ፣ ተው” ማለት የፈለግነው ሀገራችንን ስለምንወድ፣ አደጋውም ስለታየን ነው፡፡ ይኽ ሳይሆን ቀርቶ መንግስት ዐቢይና ተቀዳሚ ተግባሩን መርሳቱን ከቀጠለ ሕዝብ ራሱን እያደራጀ መከላከል ይገደዳል፤ እንዲህ ያለው አያያዝ ደግሞ ምን ሊያስከትል እንደሚችል ከታሪክም ከጎረቤቶቻችንም መማር ተገቢ ይመስለናል ሲል ገልጧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply