የጉማይዴ ህዝብን ወክለው ለአቤቱታ ወደ አዲስ አበባ የመጡ ተወካዮች ችግራቸውን ለፌደራል መንግስት ሊያሳውቁ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ  ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም…

የጉማይዴ ህዝብን ወክለው ለአቤቱታ ወደ አዲስ አበባ የመጡ ተወካዮች ችግራቸውን ለፌደራል መንግስት ሊያሳውቁ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም…

የጉማይዴ ህዝብን ወክለው ለአቤቱታ ወደ አዲስ አበባ የመጡ ተወካዮች ችግራቸውን ለፌደራል መንግስት ሊያሳውቁ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጉማይዴ ሕዝብ ከመጋቢት 2003 ጀምሮ በኮንሶ ዞን ሥር እንዲተዳደር የተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም በየደረጃው ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድምጹን ሲያሰማ መቆየቱን ይናገራሉ። ከ2011 ጀምሮ ከ80 በላይ ሰዎች ሲገደሉ 40 ሺህ ያህል እንደተፈናቀሉ ችግራቸውን ለፌደራል መንግሥት ለማሳወቅ አዲስ አበባ የመጡ የማኅበረሰቡ ተወካዮች ገልጸዋል። DW እንደዘገበው። የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ተቻችለው የሚኖሩበት ጉማይዴ እኔ ሳልፈቅድ በገዥዎች ብያኔ ተጨፍልቂያለሁ በሚል ተቃውሞ ማንሳቱን ተከትሎ በብዙ አመረሰሮች ዘንድ ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑ ተገልጧል። በጉማይዴ፣በሰገን፣በኮንሶ፣አሌና ደራሼ አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት የመንግስት አካላት በሚደግፏቸው ታጣቂዎች በሚፈፅሟቸው ጥቃቶች ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ እና ቁሳዊ እልቂት እያስከተለ መሆኑ ይታወቃል። ጥቅምት 6 እና 7 ቀን 2013 በአማሮ ወረዳ በአመሰራዎች ላይ አነጣጥሮ፣በኮንሶ ደግሞ አማራን ጨምሮ በሌሎች ብሄር ተወላጆች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ በመፈፀሙ በርካቶች መገደላቸውና መቁሰላቸው እንዲሁም ሽዎች መፈናቀላቸው ይታወቃል። ሽህዎች አሁንም በመጠለያና በእርዳታ ችግር እየተሰቃዩ መሆኑ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply