የጉማይዴ ማህበረሰብ ጥያቄ የወረዳ መዋቅር እንጅ የክልልነት እንዳልሆነ ተገለጸ

የጉማይዴ ማህበረሰብ በሚኖርበት አካባቢ የሰላም እና የመልካም አስተዳደር እጦት ዉስጥ በመሆኑ የክልል እና የፌደራል መንግስት የወረዳ መዋቅር እንዲተገበርለት ጥያቄዉን ባዋቀረዉ የሰላም ኮሚቴ በኩል ማቅረቡን የጉማይዴ የሰላም ኮሚቴ አባል አቶ ሰብስቤ መሸሻ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡

ጉማይዴ በደብብ ክልል ከኮንሶ ዞን፤ ደራሼ፤ አማሮ፤ ቡርጅ ልዩ ወረዳዎች ጋር የሚዋሰን እና ከ145 ሺ በላይ ህዝብ የሚኖርበት አካባቢ መሆኑን የጉማይዴ ሰላም ኮሚቴ አስታዉቋል፡፡

የጉማይዴ ማህበረስብ ጥያቄ የሰላም የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር እንጂ ሌላ የተለየ እና በአንዳንዶች እንደሚናፈሰዉ የክልልነት ጥያቄ አይደለም ብለዋል የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሰብስቤ መሸሻ  ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ ስብስቤ ገለጻ በተቋቋመዉ የሰላም ኮሚቴ አማካኝነት ጥያቄዉን ከኮንሶ ዞን ጀምሮ እሰከ ፌደራል ድረስ ያቀረቡ ቢሆንም በወረዳ እና በዞን ያሉ አመራሮች ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ከማስተናገድ ይልቅ እንግልት እና መፈናቀሎች በማህበረሰቡ ላይ እንዲደርስ እያደረጉ መሆኑን ነው፡፡

በተለይ በአካባቢዉ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በትግራይ ክልል ላይ በነበረዉ የህግ ማስከበር ዘመቻ ከቦታዉ በተነሱበት ወቅት በርካታ የጉማይዴ ማህበረሰቦች እንግልት እና ጥቃት ስላጋጠማቸዉ ከ40 ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ወደ አጎራባች ከተሞች እና ቀበሌዎች መፈናቀላቸውን ሰብሳቢው ተናግረዋ፡፡

**************************************************************************

ዘጋቢ፡ ቤዛዊት ግርማ

ቀን 21/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply