የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ያሳለፈውን “የክልል እንሆናለን” ውሳኔ ውድቅ መደረጉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሰሞኑ በጉራጌ…

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ያሳለፈውን “የክልል እንሆናለን” ውሳኔ ውድቅ መደረጉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሰሞኑ በጉራጌ ዞን ዋና ከተማ ወልቂጤን ጨምሮ በተለያዩ የወረዳ ከተሞች ህዝቡ እያነሳው ላለው የክልል እንሁን ህገ መንግስታዊ እና ሰላማዊ ጥያቄ መንግስት የሰጠው ምላሽ አፋኝ መሆኑን በመግለጽ ለቀናት የስራ ማቆም አድማ ተደርጓል። የጉራጌ ዞን ምክር ቤትም አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት በመንግስት በኩል በቀረበው የክላስተር አደረጃጀትና በህዝብ በኩል እየተጠየቀ ያለውን የክልል እንሁን ጥያቄን በአጽንኦት ከተመከለተ በኋላ የክላስተር አደረጃጀትን ውድቅ ማድረጉ ይታወቃል። ከውሳኔው ጋር በተያያዘ የጉራጌ ህዝብ እና የጉራጌ ወዳጆች ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ድጋፍ መስጠታቸውና ብዙዎች በአደባባይ ወጥተው ደስታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎም የቡታጅራ ከተማ በ2014 ዓ.ም 4ኛ ዙር፣ የመስቃን ወረዳ በ2014 ዓ.ም 2ኛ ዙር፣ የምስራቅ መስቃን ወረዳ በ2014 ዓ.ም በ2ኛው ዙር፣ የማረቆ ብሔረሰብ ደግሞ በ2014 ዓ.ም 4ኛ ዙር አስቸኳይ የምክር ቤት ስብሰባ አካሂደዋል። ከአጎራባች የዞን መስተዳድሮች ጋር በክላስተር በአንድ የጋራ ክልል ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በመደገፍ የጉራጌን ህዝብ እና የዞኑን ም/ቤት የክልል እንሁን ጥያቄንና ውሳኔን ውድቅ ማድረጋቸው ተገልጧል። በተመሳሳይ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳም በተወካዮቹ በኩል የክላስተር አደረጃጀቱን ደግፏል። የዞኑን ምክር ቤት ውሳኔም አገር ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ፣ የህዝቦችን የዘመናት አብሮነትና የልማት ተጠቃሚነትን የሚፃረር ሲሉ የየምክር ቤቶቹ አባላት ኮንነዋል። ከአጎራባች የዞን መስተዳድሮች ጋር በክላስተር በክልል ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ምክረ ሃሳብም ፍትሃዊ ተጠቃሚነትንና የዜጎችን አብሮነት የሚያስቀጥል እንደሆነ በምክር ቤት አባላት ተንጸባርቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል። በጉራጌ በኩል ግን አሁንም እያቀረብነው ያለው ጥያቄ ሰላማዊ እና ህገ መንግስታዊ በመሆኑ የኃይልንና ሌሎች ያልተገቡ ጨፍላቂ አካሄዶችን በመተው መንግስት በአስቸኳይ ተገቢ ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል የሚል አቋም ይዘው እየታገሉ ይገኛሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply