የጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ጀማል ከኃላፊነታቸው ተነሱ 

በሃሚድ አወል

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አቶ መሐመድ ጀማልን ከዞን አስተዳዳሪነት አንስቶ በምትካቸው አቶ ላጫ ጋሩማን አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ። የዞኑ ምክር ቤት አስተዳዳሪውን ያነሳው ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 14፤ 2015 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው።

በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባ የአዲሱን አስተዳዳሪ ሹመት ለምክር ቤት ያቀረቡት፤ የጉራጌ ዞን የመንግስት ተጠሪ እና የብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ መሆናቸውን አንድ የዞኑ ምክር ቤት አባል “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። አቶ መሐመድ ጀማል ከኃላፊነታቸው የተነሱት “ባቀረቡት ጥያቄ እና የዞኑን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ” መሆኑን አቶ ክፍሌ መናገራቸው እኚሁ የምክር ቤቱ አባል ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ፤ የአዲሱ አስተዳዳሪ ሹመት የጸደቀው በዘጠኝ ድምጸ ተዓቅቦ መሆኑን በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። (ኢትዮጵያ አንሳይደር)

[ይህ ዘገባ ዝርዝር መረጃ ይታከልበታል]

The post የጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ጀማል ከኃላፊነታቸው ተነሱ  appeared first on Ethiopia Insider.

Source: Link to the Post

Leave a Reply