የጉራ ፈርዳ ወረዳ ከአሁን ቀደም በተደጋጋሚ ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች ከዞንና ከክልል አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ታጣቂዎች በንፁሃን ላይ ጥቃት በመፈፀም ከፍተኛ ጉዳት በማስከተል 3 ቀበሌዎችን ተቆ…

የጉራ ፈርዳ ወረዳ ከአሁን ቀደም በተደጋጋሚ ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች ከዞንና ከክልል አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ታጣቂዎች በንፁሃን ላይ ጥቃት በመፈፀም ከፍተኛ ጉዳት በማስከተል 3 ቀበሌዎችን ተቆ…

የጉራ ፈርዳ ወረዳ ከአሁን ቀደም በተደጋጋሚ ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች ከዞንና ከክልል አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ታጣቂዎች በንፁሃን ላይ ጥቃት በመፈፀም ከፍተኛ ጉዳት በማስከተል 3 ቀበሌዎችን ተቆጣጥረዋል ሲል በጻፈው ደብዳቤ ወቀሰ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር ስር የሚገኘው የጉራ ፈርዳ ወረዳ ከጥቅምት 2013 ጀምሮ የሸኮ፣የሜኢኒትና የመዥንገር ታጣቂዎች በጋራ በመሆን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እየፈፀሙበት ይገኛል። በዚህም በርካታ ንፁሃን ተገድለዋል፤ ከፍተኛ ሀብት ንብረት ወድሟል፣ ተቃጥሏል። ታጣቂዎቹ በተለይም በአማራ ላይ ከፍተኛ የጅምላ ፍጅት በመፈፀም ሹፒ፣ቤኒቃ እና ሌላ አንድ ቀበሌዎችን መቆጣጠራቸው እየተነገረ ነው። ይህን ተከትሎም የጉራ ፈርዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ሻሎ ነገሩ ከአቅማችን በላይ ነው በሚል ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በአሚማ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም ወረዳው መጋቢት 17 ቀን 2013 ለቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት በጻፈው ደብዳቤ የፀጥታ ችግሩ በአስቸኳይ እንዲፈታ በሚል ከአሁን ቀደም በተደጋጋሚ ላደረገው የእርዳታ ጥሪ ምላሽ ፈጣን ምላሽ አልሰጡም ሲል ወቅሷል። መስተዳደሩ በደብዳቤው ከአንድ ቀበሌ ጥቃት የጀመረው ታጣቂ ቡድኑ 3 ቀበሌዎችን ተቆጣጥሮ ወደ 6 ቀበሌዎች ለመያዝ እየተንደረደረ መሆኑን አስታውቋል። በመሆኑም መጋቢት 16 ቀን 2013 በገሊማ ቀበሌ ነዋሪ በሆኑ በ7 ሚሊሻዎችና በአርሶ አደሮች ላይ ታጣቂዎች የፈፀሙትን ግድያ ተከትሎ የቤንች ሸኮ ዞን ከክልል ጋር በመነጋገር የመከላከያ ሰራዊት እንዲመድብ፣ ለሚሊሻዎች ትጥቅ እንዲያሟላ፣ የጥይት እጥረት እንዲያስተካክልና የስራ ማስኬጂያ ገንዘብም ድጋፍ እንዲደረግለት ጠይቋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ለእርዳታ ጥያቄያችሁ ምን ምላሽ ተሰጣችሁ ሲል የወረዳው ዋና አስተዳዳሪን አቶ ሲሳይ ሻሎን አነጋግሯል። አቶ ሲሳይ እንዳሉት ከሆነ በትናንትናው እለት የመከላከያ ሰራዊት ገብቷል፤ በሹፒ ቀበሌም የተወሰነ ቦታ ይዟል። ወደ አሮጌ ብርሃንና ገሊማ ቀበሌዎችም በቂ ኃይል እየገባ መሆኑን የገለፁት አቶ ሲሳይ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል። በመጨረሻም አቶ ሲሳይ ለዞንና ለሚመለከተው አካል ላቀረብነው ጥያቄ ፈጣን ምላሽ በመስጠታቸው እናመሰግናለን ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply