#የጉሮሮ #አለርጂ እና ህክምናውየጉሮሮ አለርጂ በህክምና ሊድን የሚችል የጤና እክል ቢሆንም ተገቢውን የህክምና ክትትል ካልተደረ ግን ለዜጎች ህይወት አስጊ መሆኑ ይገለጻል፡፡ዶክተር ይበልጣል…

#የጉሮሮ #አለርጂ እና ህክምናው

የጉሮሮ አለርጂ በህክምና ሊድን የሚችል የጤና እክል ቢሆንም ተገቢውን የህክምና ክትትል ካልተደረ ግን ለዜጎች ህይወት አስጊ መሆኑ ይገለጻል፡፡

ዶክተር ይበልጣል ተሾመ ከአንገት ባላይ ሃኪም ናቸው ፤ በጣም ከተለመዱ እና የብዙዎች የጤና እክል ከሆኑት ህመሞች መካከል አንዱ የጉሮሮ አለርጂ መሆኑ ይናገራሉ፡፡

#ለጉሮሮ አለርጂ ህመም መነሻ #ምክንያቶች

• የአየር መለዋወጥ ወይም መቀየር
• የሰዎች ተፈጥሮ
• አካባቢ እንደ አዋራ፣ ብናኝ ፣ ጭስ
• አንዳንድ ምግቦች ለጉሮሮ አለርጂ መከሰት እንደ መነሻ ምክንያት ሊጠቀሱ እንደሚችሉ ተመላክቷል፡፡

#የሚስተዋሉ ምልክቶች

• በጉሮሮ አከባቢ የመከርከር ስሜት መኖር
• የጉሮሮ ማሳከክ
• የድምጽ መለወጥ (መጎርነን)
• ለመተንፈስ መቸገር
• ሰውነት መነፋፋት
• አይን የማሳከክ አይነት ስሜቶች በታማሚው ላይ ሊስተዋሉ ይችላል ተብሏል።

#ህክምናው

በሃኪም የሚታዘዝ መድሃኒት መኖሩን ባለሞያው የነገሩን ሲሆን፤ በቅድሚያ ህመሙ የሚነሳበትን ምክንያት ማወቅ የጉሮሮ አለርጂን ቀድሞ ለመከላከል እንደሚረዳ ተነግሯል፡፡

#በቤት ውስጥ ህመሙን እንዴት #ማስታገስ ይቻላል?

• የመኖሪያ አከባቢ ንጽህናን መጠበቅ
• በተቻለ መጠን ለጭስ፣ ለአዋራ እና
ብናኝ ተጋላጭ አለመሆን
• ጉሮሮን በጨው እና ለብ ባለ ውኃ መጉመጥመጥ
• ማስቲካ ማኘክ እና ከረሜላ መምጠት
• በቋሚነት የአካል ብቃት እቅስቃሴ ማድረግ
• በየቀኑ ውሃ መጠጣት እና አንድ ማንኪያ ማር ጠዋት እና ማታ መዋጥ
• አልኮል እና ቡና አብዝቶ አለመጠቀም
•የአየር መቀየር ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑ ተነግሯል።

የጉሮሮ አለርጂ ከተከሰተ እና ምልክቶች የሚስተዋሉ ከሆኑ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ የህክምና አገልግሎትን ማግኘት ሁኔታው የከፋ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ቀድሞ ለመከላል ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ተብሏል።

በእሌኒ ግዛቸው

ሚያዝያ 07 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply